ስፓርት
አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ሲዳማ ቡና በይፋ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን ላለፈው አንድ ዓመት ሲያሰለጥን የቆየው አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ምክትላቸው ቾንቤ ገብረህይወት ከሲዳማ ቡና ጋር ተለያይተዋል።
የሲዳማ ቡና ዋና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ምክትላቸው ቾንቤ ገብረህይወት ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ቾንቤ ገብረህይወት በክለቡ በነበሩበት ወቅት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል፡፡
Read More...
በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች በተደረገው ውድድር የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸነፉ፡፡
በቤይሩት ማራቶን በወንዶች ጋዲሳ ጣፋ 02፡10፡34 በመግባት የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ጎጃም በላይነህ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡
እንዲሁም በሴቶች በተደረገው…
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ቡድን ማሊን 2 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ቡድን ማሊን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡
ቡድኑ ከሜዳው ውጪ ባደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ነው 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸነፈው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የማሸነፊያ ግቦች እሙሽ ዳንኤል እና ንግስት በቀለ አስቆጥረዋል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ የመልስ ጨዋታውን የፊታችንእሑድ…
በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል እና ማንቼስተር ዩናይትድ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች አርሰናል እና ማንቼስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ቶትንሃም ተሸንፏል፡፡
በሜዳው በርንሌን ያስተናገደው አርሰናል ትሮሳርድ፣ ሳሊባ እና ዚንቼንኮ ባስቆጠሯቸው ግቦች 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በተመሳሳይ በኦልድ ትራፎርድ ሉተን ታዎንን…
የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የውድድር ዘመን ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የውድድር ዘመን ነገ በሚደረጉ ስድስት ጨዋታዎች ጅማሮውን እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ዘንድሮ በሁለት ምድቦች 28 ክለቦችን ተሳታፊ የሚያደርገው ውድድሩ በሐዋሳ እና አዲስ አበባ የሚከናወን መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ከውድድሩ ቀደም ብሎም በሁለቱም ምድቦች የውድድር አመራሮች እና ተሳታፊ ክለቦች…
ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሚሳተፉ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ላለበት ወሳኝ ጨዋታ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ከሴራሊዮን እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ የሚያሰልፏቸውን 23 ተጫዋቾች መለየታቸውንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ህዳር ወር መጀመሪያ…
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የክለቦች ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ሊግ እና የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የክለቦች ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡
በዚህ ድልድል በምድብ ሀ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀምበሪቾ ዱራሜ፣ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ወላይታ ድቻ ከደሴ ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ከሃላባ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ፣ ነገሌ አርሲ ከስልጤ…