Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኤቨርተን የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ የፋይናንስ ህግን ተላልፎ በመገኘቱ 10 ነጥብ ተቀነሰበት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ የፋይናንስ ህግን ተላልፎ በመገኘቱ 10 ነጥብ ተቀንሶበታል፡፡ ክለቡ በ2021-22 የውድድር ዘመን ከፋይናንስ ጥሰት ጋር በተያያዘ በገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ ምርምራ ሲደረግበት መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ በተደረገው ማጣራትም በፋይናንሻል ፍትሃዊነት የተቀመጠውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ህግ ተላልፎ የተገኘው ኤቨርተን 10 ነጥብ እንዲቀነስበት ቅጣት ተላልፎበታል፡፡ በሊጉ የፋይናንስ ህግ መሰረት ክለቦች እንደዚህ አይነት ጥሰት ሲፈፅሙ በሶስት…
Read More...

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የምንጊዜም ጎል አስቆጣሪነት ሪከርዱን አሻሻለ

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትናንት ምሽት ጎል ማስቆጠሩን ተክትሎ የብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ጎል አስቆጣሪነት ሪከርዱን 128 አድርሷል፡፡ ሮናልዶ ትናንት ምሽት በዩሮ 2024 ማጣሪያ ፖርቹጋል ሌችተንስታይንን 2 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ በ46ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥሯል፡፡ ይህን ተክተሎም የ38 ዓመቱ አጥቂ ለፖርቹጋል 204 ጊዜ…

በድሬዳዋ ወጣቶች የእግር ኳስ ጥበብ የሚቀስሙበት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ዋና ፀሐፊ ማዳም ፋጡማ ሳሞራ ወጣቶች የእግር ኳስ ጥበብን በትምህርት ቤቶች የሚቀስሙበትን "እግር ኳስ -ለትምህርት ቤቶች" ፕሮጀክት በድሬዳዋ ይፋ አደረጉ። ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በእግር ኳስ ዘርፍ ያላትን ደረጃ ለማሳደግና ተተኪ ወጣቶች በእግር ኳስ ጥበብ መሠረታዊ ዕውቀት እንዲጨብጡ ያግዛል…

ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን በአቻ ውጤት ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከሴራሊዮን አቻው ጋር አከናውኗል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ተደርጓል፡፡ ጨዋታው በተከሰተ ጭጋጋማ…

የፊፋ ዋና ፀሐፊ ለሥራ ጉብኝት ድሬዳዋ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ዋና ፀሐፊ ፋጡማ ሳሞራይ ለሥራ ጉብኝት ማምሻውን ድሬዳዋ ገብተዋል፡፡ ዋና ፀሐፊዋ ማምሻውን ድሬዳዋ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ዋና ፀሐፊዋ በድሬዳዋ ቆይታቸው የሕፃናት…

አትሌት ትዕግስት በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ውስጥ ተካተተች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ማራቶን የክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎች ውስጥ ተካትታለች፡፡ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት ዘርፍ ቀደም ሲል 11 ዕጩዎች ለምርጫ የቀረቡ ሲሆን÷የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ የመጨረሻዎቹን አምስት እጩዎች ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ ዝርዝር ውስጥም…

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእግር ኳስ ፌደሬሽን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብርን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ መሰረትም ፕሪሚየር ሊጉ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡ በዕለቱም ልደታ ክፍለ ከተማ ከአርባ…