Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በጀርመን በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን ካርልስሩህ በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በ3 ሺህ ሜትር በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አምስት ተከታትለው በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡ አትሌት ለምለም ኃይሉ 8 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ከ55 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ውድድሩን በአንደኝነት ያሸነፈችው። አትሌት ወርቁውሃ ጌታቸው 8 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ከ98 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ዳዊት ስዩም 8 ደቂቃ…
Read More...

ካፍ ለቻን ውድድር አሸናፊ የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት አሳደገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የቻን ውድድር አሸናፊ ለሚሆነው ሀገር የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት መጠን ማሳደጉን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ የአፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሙትሴፔ እንደገለፁት ፌደሬሽኑ ለቻን አሸናፊ ሀገር የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት 60 በመቶ መጨመሩን…

ለ44ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና አትሌቶች ልምምድ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ የካቲት 18 ቀን 2023 በአውስትራሊያ ባትረስት ከተማ ለሚካሄደው 44ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ልምምድ እያደረጉ ነው፡፡ በውድድሩ ኢትዮጵያን የሚወክሉ 14 ወንድና 14 ሴት አትሌቶች ከነተጠባባቂዎቹ ከ40ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በወጣትና በአዋቂ ምድብ…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተቋርጦ የሚጀመርበት ቀን ለአንድ ሣምንት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከተቋረጠበት የሚጀመርበት ቀን ለአንድ ሣምንት ተራዘመ፡፡ በአዳማ ከተማ የሚካሄደው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር መግለጹ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጅ ውድድሩ የሚጀመርበት ቀን ቀድሞ ከተገለፀው…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥር 20 ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለቻን ላለበት ውድድር ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር ከፊታችን ጥር 20 ቀን ጀምሮ በአዳማ ከተማ መካሄዱ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡ በዚህ መሰረትም ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች የ12ኛ ሳምንቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሁም…

ለአትሌት ታምራት ቶላ የምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለአትሌት ታምራት ቶላ የምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡ ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ለ46 አትሌቶቹ የተለያዩ ማዕረጎችን ሰጥቷል፡፡ በዚህም በኦሪገን ማራቶን ሻምፒዮን የነበረው አትሌት ታምራት ቶላ የዋና ሳጅን ማዕረግ የነበረው ሲሆን÷ በዛሬው ዕለት የምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ…

የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን-አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናገሩ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን በዛሬው እለት ከሊቢያ አቻው ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ አስመልክተው  አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አማካዩ ጋቶች ፓኖም  መግለጫ ሰጥተዋል፡፡…