ስፓርት
ጋሬዝ ቤል ከእግር ኳስ ሕይወትራሱን አገለለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል ጋሬዝ ቤል ራሱን ከክለብና ከብሄራዊ ቡድን ማግለሉን አስታውቋል፡፡
ቤል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ÷ “የምወደውን የእግር ኳስ ስፖርት የመጫወት ህልሜን በማሳካቴ እድለኛ ነኝ ፤ነገር ግን ከዚህ በላይ በእግር ኳስ ሕይወት አልቀጥልም ብሏል፡፡”
የቀድሞው የቶተንሃም እና የሪያል ማድሪድ ኮከብ በዌልስ ብሄራዊ ቡድን 16 ዓመታትን ያሳለፈ ሲሆን÷ 111 ጨዋታዎችን አድርጎ 41 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡
Read More...
ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኑ፡፡
ስፔናዊው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ÷ በዓለም ዋንጫው የተሰናበቱትን አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ በመተካት ነው በዛሬው ዕለት የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት፡፡
የፖርቹጋል እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ፈርናንዶ…
አትሌት ሰለሞን ባረጋ በስፔን ኤልጎይባር አገር አቋራጭ ውድድር አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሰለሞን ባረጋ በስፔን ኤልጎይባር ሁዋን ሙጌርዛ በተደረገ የ10 ኪሎ ሜትር የአገር አቋራጭ ውድድር አሸነፈ፡፡
አትሌት ሰሎሞን ርቀቱን በ33 ደቂቃ ከ14 ሴኮንድ በመጨረስ ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል፡፡
በርቀቱ ትውለደ ኢትዮጵያዊው እና ለባህሬን የሚሮጠው ብርሃኑ ባለው 2ተኛ ሲሆን÷ ስፔናዊው አዴል ሜካል 3ኛ ሆኖ…
አማኑኤል ኢሳያስ ኢንተርናሽናል የቮሊቦል ኢንስትራክተር ደረጃን አገኘ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ለአማኑኤል ኢሳያስ ኢንተርናሽናል የቮሊቦል ኢንስትራክተርነት ደረጃን ሰጠ።
በዚህም ከአንጋፋው ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር አለማየሁ ሸዋታጠቅ ቀጥሎ አማኑኤል ኢሳያስ ሁለተኛው ኢትዮጵያውያዊ ሆኗል፡፡
አማኑኤል በአሁኑ ሰዓት ሶስተኛ ደረጃ የቮሊቦል አሰልጣኝነት የምስክር ወረቀት ያለው ብቸኛ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ አቻው ጋር ምሽት 1ሰዓት የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ቡድኑ ከሞሮኮ ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ራባት መሐመድ ስድስተኛ እግር ኳስ አካዳሚ ተገኝቷል።
ጨዋታውም ምሽት 1 ሰዓት እንደሚጀመር ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለቻን ዝግጅት ሞሮኮ…
አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድር ልትመለስ ነው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ ጥር 15 በሚካሄደው 22ኛው የአራምኮ ሂዩስተን የግማሽ ማራቶን ውድድር የርቀቱ የምንጊዜም ታላቅ ሯጮች መካከል አንዷ የሆነችው ጥሩነሽ ዲባባ ትሳተፋለች፡፡
የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ እና የአምስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮና አሸናፊዋ አትሌት ጥሩነሸ ዲባባ በግማሽ ማራቶን 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ የግሏ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሞሮኮ የሚያደርገውን ጉዞ ጀምሯል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ውድድር ዝግጅት ወደ ሞሮኮ የሚያደርገውን ጉዞ ጀምሯል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ወደ ግብፅ ካይሮ በረራ ያደረገ ሲሆን ፥ ቡድኑ ከደቂቃዎች በፊት በሰላም ካይሮ መድረሱ ታውቋል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ለትንሽ ደቂቃዎች በካይሮ አየር ማረፍያ ቆይታ ካደረገ በኋላም ወደ ሞሮኮ ጉዞውን የሚቀጥል መሆኑን…