ስፓርት
ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድደር ኢትዮጵያ ዩጋንዳን አሸነፈች
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድደር ኢትዮጵያ ዩጋንዳን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡
የኢትዮጵያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ከድር ዓሊ ጨዋታው በተጀመረ 60ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ምድቧን በ4 ነጥብ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።
ብሔራዊ ቡድኑ ለግማሽ ፍፃሜው ከደቡብ ሱዳን ጋር የፊታችን ማክሰኞ ጥቅምት 29 ቀን የሚጋጠም ይሆናል፡፡
Read More...
በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ድቻ እና ወልቂጤ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ድሬዳዋ ላይ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
10 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ እና መቻል ባደረጉት ጨዋታ ወላይታ ድቻ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግብ ቃልኪዳን ዘላለም በ31ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገ…
በፕሪሚየር ሊጉ ባህር ዳር እና ድሬዳዋ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሣምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ድሬዳዋ ላይ በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል።
10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከባሕር ዳር ባደረጉት ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ባለ ድል ሆኗል።
በጨዋታው ባሕርዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ2 አሸንፏል፡፡
የማሸነፊያ ጎሎችን ተስፋዬ ታምራት፣ ፉዐድ ፈረጃ እና…
የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በድሬዳዋ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ6ኛ እስከ 10ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም ይጀመራል።
በቀጣዮቹ 5 ሳምንታት በድሬዳዋ የሚካሄዱት ጨዋታዎች የሰዓት ማሻሻያ የተደረገባቸው ሲሆን÷ጨዋታዎቹ 10 ሰዓት እና ምሽት 1 ሰዓት የሚካሄዱ ይሆናል።
በመርሐ ግብሩ መሰረትም ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ…
ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በአቻ ውጤት ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ሁለት አቻ ተለያዩ፡፡
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ያደርጋል፡፡
ሊግ ኩባንያው በ5ኛ ሳምንት በተስተዋሉ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ በ5ኛ ሳምንት በተስተዋሉ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡
የኩባንያው ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ-ስርዓት ባደረገው ስብሰባ በ5ኛ ሳምንት በተደረጉ ውድድሮች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የሥነ ምግባር ሪፖርት በመመርመር የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በተጫዋቾች…
በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የባህር ዳር ቆይታን የሚቋጨው ተጠባቂ ጨዋታ ዛሬ 10 ሰዓት ተካሂዷል፡፡
በጨዋታው ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡