ስፓርት
በፓን አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ ትምህርት ቤቶች ታወቁ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 ( ኤፍ ቢ ሲ) ገዳ ሮበሌ አንደኛ ደረጃ እና አዋሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በፓን አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚወዳደሩ ታውቋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ከ16 አመት በታች የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ የማጣሪያ ውድድር ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በውድድሩም ኢትዮጵያን ወክለው በወንዶች ገዳ ሮበሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም በሴቶች አዋሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ክልል አሸናፊ በመሆን መለየታቸውን…
Read More...
የፓን አፍሪካኒዝም ሻምፒዮን የተማሪዎች የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው የፓን አፍሪካኒዝም ሻምፒዮን የተማሪዎች የእግር ኳስ ውድድር በአዳማ ከተማ ተጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሃግብሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና ፀሃፊ ባህሩ ጥላሁን ÷ የፓን አፍሪካኒዝም ሻምፒዮን ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት አንፃር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
የባህልና ስፖርት…
40ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱሉልታ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 40ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ተጠናቋል፡፡
በማጠናቀቂያ መርሐ ግበሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ፕሬዚዳንት ጄነራል ጃክሰን ትዊ…
አትሌት ለተሰንበት ግደይ የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮን ሆነች
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለምሻምፒዮና የ10ሺህ ሜትር አሸናፊዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮናን አሸነፈች፡፡
ውድድሩ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ለ40ኛ ጊዜ በሱሉልታ ሲካሄድ የአለም ቻምፒዮኖች፣ የኦሊምፒክ ኮከቦችና ሌሎች ጠንካራ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡
የጃንሜዳን የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር…
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲ አረቢያውን አል-ናስር ተቀላቀለ
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲ አረቢያውን ክለብ አል ናስርን ተቀላቀለ።
የ37 አመቱ ሮናልዶ ከእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ከተለያየየ በኋላ አል ናስርን ለመቀላቀል መስማማቱ የሚታወስ ነው።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቢቆይም የመጨረሻ ማረፊያው የሳዑዲው ክለብ ሆኗል።…
ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት እንደሚቀረፍ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት እንደሚቀረፍ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ስራ አቁመው የነበሩ የስኳር ፋብሪካዎች ምርት ማምረት መጀመራቸውን ተከትሎ ነው ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት ይቀረፋል የተባለው፡፡
በጸጥታ ችግር እና በመለዋወጫ እጥረት ምክንያት የስኳር…
ብራዚል በኳስ ንጉሡ ፔሌ ሕልፈት ምክንያት 3 የሐዘን ቀናት አወጀች
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳስ ንጉሡ ፔሌ ሕልፈት ምክንያት ብራዚል ሦስት የሐዘን ቀናት አወጀች፡፡
የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ የ82 ዓመቱን የኳስ ንጉሥ ፔሌ ሕልፈት ተከትሎ ሦስት ተከታታይ የሐዘን ቀን አውጀዋል።
ብራዚላውያን በምንጊዜም ኮከባቸው ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን እየገለጹ ነው።
ፔሌ ከሀገሩ ብራዚል ጋር ሶስት የዓለም…