ስፓርት
የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በለተሰንበት ግደይ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በለተሰንበት ግደይ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደረገ።
በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች በመጨረሻዎቹ ሰከንዶች ለተሰንበት ግደይ ሄለን ኦቢሪን በክርን መታታለች በሚል ኬንያ ለዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቅሬታ አስገብቷል፡፡
ይሁን እንጅ ለተሰንበት ሄለንን በውድድሩ ፍፃሜ አካባቢ ቀድማት የነበረ በመሆኑንና አትሌቷ ዙሩን በበላይነት የማጠናቀቅ እድሏ ከፍተኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ክሱ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ከአፍሪካ ስፖርት ያገኘነው መረጃ…
Read More...
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሦስት የፍጻሜ ውድድሮች ትሳተፋለች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ኢትዮጵያ በሦስት የፍጻሜ ውድድሮች ትሳተፋለች፡፡
በዚህም መሰረት ቀን 10:15 በሚካሄደው የሴቶች ማራቶን ፍጻሜ ጎይቲቶም ገብረስላሴ፣ አባበል የሻነህ እና አሸቴ በከሪ ይሳተፋሉ፡፡
ሌሊት 11፡20 በሚካሄደው የወንዶች 3 ሺህ…
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ኡጋንዳ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ኡጋንዳ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።
ውድድሩን ኡጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጌ አሸንፏል።
እስከ ፍፃሜው ብርቱ ፉክክር ካደረጉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች መካከል ሰለሞን ባረጋ አምስተኛ እና በሪሁ አረጋዊ ሰባተኛ በመሆን አጠናቀዋል።
ኬንያዊ እና ኡጋንዳዊ…
የዓለም የወንዶች ማራቶን ፍጻሜ ውድድርን አትሌት ታምራት ቶላ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች ማራቶን የፍጻሜ ውድድርን አትሌት ታምራት ቶላ አሸነፈ፡፡
አትሌት ታምራት ቶላ 2 ሰዓት ከ 5 ደቂቃ ከ 36 ሰከንድ በመግባት ነው ውድድሩን ያሸነፈው፡፡
አትሌት ሞስነት ገረመው ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድርሩን አጠናቋል፡፡
በውድድሩ…
የወንዶች ማራቶን የፍጻሜ ውድድር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወንዶች ማራቶን የፍጻሜ ውድድር በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በውድድሩም÷ አትሌት ሌሊሳ ደሲሳ፣ አትሌት ሙስነት ገረመው፣ አትሌት ሰይፉ ቱራ እና አትሌት ታምራት
ቶላ ተሳትፈዋል፡፡
በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡…
በኦሬገን ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ማራቶንና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ይጠበቃሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ማራቶን እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ይጠበቃሉ።
ቀን 10 ሰዓት ከ15 ላይ የወንዶች ማራቶን የሚካሄድ ሲሆን፥ ሌሊሳ ደሲሳ፣ ሙስነት ገረመው፣ ሰይፉ ቱራ እና ዓየለ ቶላ ይሮጣሉ።
ምሽት 5 ሰዓት ላይም የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ይካሄዳል።…
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሊቱን በተካሄዱ የወንዶችና ሴቶች 1ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያዎች በሴቶች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች አልፈዋል፡፡
ጉዳፍ ጸጋይ 4፡01.28 ከምድብ አንድ 1ኛ፣ ፍረወይኒ ኃይሉ 4፡02.28 ከምድብ አንድ 4ኛ፣ ሂሩት መሸሻ 4፡04.05 በሆነ ጊዜ ከምድብ ሁለት 2ኛ በመሆን አልፈዋል፡፡…