ስፓርት
በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ አትሌት ወርቅውኃ ጌታቸው አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌሊት ላይ በሞናኮ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ የ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር አትሌት ወርቅውኃ ጌታቸው አሸነፈች፡፡
በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር አትሌት ወርቅውኃ ጌታቸው 9 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ19 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት አንደኛ ስትወጣ÷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ደግሞ 9 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ሆና ጨርሳለች፡፡
በሌላ መርሐ ግብር በወንዶች 3 ሺህ ሜትር÷ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 7 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ ከ81 ማይክሮ…
Read More...
የካፍ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ ሱፐር ሊግ ውድድርን ይፋ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ከፊፋው አቻቸው ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ጋር በመሆን የአፍሪካ ሱፐር ሊግ ውድድርን በዛሬው እለት ይፋ አድርገዋል፡፡
ውድድሩ ይፋ በሆነበት ወቅት የታንዛኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቃሲም ማጃሊዋ ተገኝተዋል፡፡
ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ 24 ቡድኖችን የሚያሳትፈው የአፍሪካ…
ፈረሰኞቹ በቻምፒየንስ ሊጉ ቅድመ ማጣሪያ ከሱዳኑ አልሂላል ጋር ይጫወታሉ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሱዳኑ አልሂላል ጋር እንደሚያደርግ ታውቋል።
ዛሬ ካይሮ ላይ በወጣው የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ እጣ አወጣጥ ፕሮግራም መሠረት ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሜዳቸው ያደርጋሉ።
ቡድኑ በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ጨዋታው ከደቡብ ሱዳን…
አቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዝውውሩን አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና የዋሊያዎቹ አጥቂ አቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዝውውሩን ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡
አቡበከር ከወራት በፊት ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት ወደ ደቡብ አፍሪካ ቢያቀናም ዝውውሩ በፊፋ ሳይረጋገጥ ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ አጥቂው በዛሬው ዕለት…
ኢትዮጵያ የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን 3ኛ በመሆን አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ የተካሄደውን የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስተኛ በመሆን አጠናቀቀች።
በውድድሩ ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።
በሻምፒዮናው ማጠናቀቂያ እለት አራት ወርቅ እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።
በሻምፒዮናው…
በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።
በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍፃሜ ውድድር የተሳተፈው አትሌት ልኬነህ አዘዘ በ7:44.06 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አምጥቷል።
ሌላው በውድድር የተካፈለው ኢትዮጵያዊ አትሌት ድርባ ግርማ…
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀምራል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከወራት እረፍት በኋላ ዛሬ ይጀመራል፡፡
ሊጉ ዛሬ ሲጀምር ክሪስታል ፓላስ ከአርሴናል ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሼልስት ፓርክ ሰታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በመርሃ ግብሩ የመጀመሪያ ሳምንት በነገው እለት ስድስት ጨዋታዎችን የሚደረጉ ሲሆን ሊቨርፑል ከፉልሃም፣ቼልሲ ከኤቨርተን እንዲሁም…