ስፓርት
ካሪም ቤንዜማ የቻምፒየንስ ሊጉ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ
አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር አጥቂ ካሪም ቤንዜማ የውድድር አመቱ የቻምፒየንስ ሊጉ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡
ፈረንሳዊው አጥቂ ክለቡ ሪያል ማድሪድ ለ14ኛ ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን በማንሳት ክብረ ወሰኑን ይዞ እንዲቆይ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል።
በመድረኩም 15 ጎሎችን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አግቢ ሆኖ ጨርሷል።
ከዚህ ባለፈም ቡድኑ የላሊጋን ዋንጫ እንዲያነሳ አስተዋፅኦ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡
Read More...
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዋልያዎቹ ስብስብ አምስት ተጫዋቾችን ቀነሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዋልያዎቹ ስብስብ አምስት ተጨዋቾችን መቀነሳቸው ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ከማላዊ እና ግብፅ ጋር ለማድረግ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከጠሯቸው 28 ተጨዋቾች አምስት ተጨዋቾችን መቀነሳቸው ታውቋል፡፡
አሰልጣኙ ከሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር…
ኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ውጤታማነቷን ለማሳደግ የውድድሮች አይነቶችን ማስፋት አለባት – አትሌት ፖል ቴርጋት
አዲስ አበባ፣ግንቦት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ውጤታማነቷን ለማሳደግ የምትሳተፍባቸውን የውድድR አይነቶች ማስፋት አለባት ሲል ታዋቂው ኬንያዊ አትሌት ፖል ቴርጋት ተናገረ።
ከአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ብርቱ ተፎካካሪዎች መካከል የነበረው ኬንያዊው አትሌት ፖል ቴርጋት በሐዋሳ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ወጣቶች የኦሊምፒክ…
የመጀመሪያው የወጣቶች ሃገር አቀፍ ኦሊምፒክ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የወጣቶች ሃገር አቀፍ የኦሊምፒክ ጨዋታ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተጀምሯል።
በጨዋታው ከአማራ ክልል ውጭ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ስፖርተኞች ተሳታፊዎች መሆናቸው ተገልጿል።
በመክፈቻ ስነ ስርአቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ…
በምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፈው ከ18 እና 20 ዓመት በታች ልዑክ አቀባበል ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ4ኛ ጊዜ በዳሬሰላም በተካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ለተሳተፈው ልዑክ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ÷ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ…
ኢትዮጵያ በታዳጊ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ሲካሄድ በነበረው የታዳጊ አትሌቶች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአሸናፊነት አጠናቀቀች፡፡
በ8 የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ሲካሄድ በቆየው ከ18 እና ከ20 አመት በታች የሆኑ ታዳጊ አትሌቶች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች፡፡
በውድድሩ ኢትዮጵያ በ17 ወርቆች፣…
ዋልያዎቹ ከሌሴቶ አቻቸው ጋር በአቻ ውጤት ተለያይተዋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሌሴቶ አቻው ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል፡፡
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሌሴቶ በ20ኛው ደቂቃ በማክሀ ቱሜሎ አማካኝነት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥራለች፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደግሞ አቻ የምታደርገውን ጎል በ61ኛ…