ስፓርት
ዑመድ ዑኩሪ የኦማኑን ክለብ ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አጥቂ ዑመድ ዑኩሪ የኦማኑን ክለብ አል-ሱዋይክ መቀላቀሉ ተገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለመከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጫወት ከሀገራችን የስፖርት ማህበረሰብ ጋር መተዋወቅ የቻለው ባለ ግራ እግሩ አጥቂ÷ 2006 ላይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እና ኮከብ ተጫዋች በመሆን ከፈፀመ በኋላ ወደ ግብፅ ሊግ ማምራቱ ይታወሳል።
በዚያም ለአል-ኢትሀድ አሌክሳንድሪያ፣ ኤንፒ፣ ኤል ኢታንግ አል አርቢ፣ ሶሞሀ እና አስዋን ክለቦች ስድስት ዓመት ከግማሽ ያህሉን በማሳለፍ፥…
Read More...
በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን ወርቅና ብር ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን ወርቅና ብር ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡
በኮሎምቢያ ካሊ እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሌሊቱን በተደረጉ የ5 ሺህ የወንዶች እና የ3 ሺህ ሜትር የሴቶች የፍፃሜ ውድድሮች ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የወርቅ እና የብር…
በሻምፒዮናው የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።
በ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ የተወዳደረው አትሌት አድሃና ካሣዬ ኬኒያዊውን አትሌት ዳንኤል ኪሞዮ ተከትሎ 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን÷ 3 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ…
የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራልየዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ የሚካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሲጀምር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ይሳተፋሉ፡፡
በዚህም መሰረት ምሽት 12: 00 ሰዓት የወንዶች 1500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር የሚደረግ ሲሆን፥ ምሽት 12:30 ደግሞ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ይካሄዳል፡፡…
የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚደረግባቸው ቀናት ተራዘሙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚደረግባቸው ቀናት መራዘማቸውን ካፍ አስታወቀ፡፡
በዚህም መሰረት በመስከረም ወር ሊደረጉ ቀጠሮ የተያዘላቸው የዋሊያዎቹ 3ኛ እና 4ኛ የምድብ ጨዋታዎች ከመጋቢት 11 እስከ 19-2015 የሚደረጉ ይሆናል፡፡
በተጨማሪ የሀገራቱ የምድቡ 5ኛ ጨዋታ ከሰኔ 5 እስከ 13 -2015 ባሉት…
ዋልያዎቹ በቻን ማጣሪያ የደቡብ ሱዳን አቻቸውን 5 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ እግር ኳስ ሻምፒዮና (ቻን) ጨዋታ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያደረገውን የመልስ ጨዋታ 5 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ።
ሰባተኛው የቻን የእግር ኳስ ጨዋታበፈረንጆቹ 2023 በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
ዋልያዎቹ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም…
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡት አትሌቶች እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚደርስ ሸልማት ተበረከተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች ከ50 ሺህ ብር እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚደርስ ሸልማት ተበረከተ፡፡
በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመዘገበውን አኩሪ ድል በማስመልከት የአትሌቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል መርሐ-ግብር በብሔራዊ ቤተ-መንግስት…