Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በዓለም ዋንጫ አውስትራሊያ ቱኒዚያን 1 ለ 0 አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር የዓለም ዋንጫ በምድብ አራት የሚገኙት ቱኒዝያ እና አውስትራሊያ የሁለተኛ ዙር ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ በዚህም አውስትራሊያ አፍሪካዊቷን ቱኒዚያን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋ ከምድቡ የማለፍ ተስፋዋን አለምልማለች፡፡ የአውስትራሊያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሚቸል ዱክ በ23ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል
Read More...

በዓለም ዋንጫው አርጀንቲና ከሜክሲኮ ወሳኙን ጨዋታ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በዛሬው ውሎ የምድብ ሶስት እና አራት ቡድኖች ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በምድብ ሶስት አርጀንቲና ከሜክሲኮ እንዲሁም በምድብ አራት ፈረንሳይ ከዴንማርክ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል። በተለይም በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ሳይጠበቅ በሳዑዲ አረቢያ…

በምድብ 1 ኔዘርላንድስ እና ኢኳዶር ነጥብ ሲጋሩ ኳታር የመጀመሪያዋ ተሰናባች ሆናለች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው ምድብ 1 ኔዘርላንድስ እና ኢኳዶር ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል። ሁለቱ ቡድኖች ምሽት 1 ሰአት ላይ ባደረጉት ጨዋታ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ፈጣን ጎል ተመዝግባለች። ጨዋታው አንድ አቻ ሲጠናቀቅ ኮዲ ጋክፖ ለኔዘርላንድስ ኤነር ቫሌንሺያ ደግሞ ለኢኳዶር ጎሎችን አስቆጥረዋል።…

ኔይማር በጉዳት ምክንያት ከሁለት የምድብ ጭዋታዎች ውጭ መሆኑ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኔይማር ጁኒየር በጉዳት ምክንያት በሁለት የምድብ ጭዋታዎች እንደማይሰለፍ ተገለፀ፡፡ ኔይማር ትናንት ምሽት ብራዚል ከሰርቢያ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ላይ ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት ነው ከሁለት የምድብ ጨዋታዎች ውጭ የሆነው፡፡ የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ዶክተሮች ከሰርቢው ጨዋታ…

በዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል ኳታርን 3ለ1 አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫ የምድብ 2 የሁለተኛ ዙር ጨዋታ  አፍሪካዊቷ ሴኔጋል  አዘጋጇን ሀገር ኳታር  3 ለ 1 አሸንፋለች፡፡ በኳታር አልቱማም ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቡሊያን ዲያ፣ ፋሙራ ዴዴሁ እና ባባ ዲየንግ  የሴነጋልን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ሞሃመድ ሞንታሪ የኳታርን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡ የቴራንጋ አንበሶቹ በኔዘርላንድስ…

በዓለም ዋንጫው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል የምትሳተፍበትን ጨምሮ አራት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡ በዚህም በምድብ ሁለት የተደለደሉት ዌልስ ከኢራን ቀትር 7 ሰዓት ላይ የሚጫወቱ ሲሆን ÷ በተመሳሳይ በዚሁ ምድብ የሚገኙት እንግሊዝ ከአሜሪካ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡ በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር በምድብ አንድ…

በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ፖርቹጋል ጋናን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ ጨዋታ የአምስተኛ ቀን ውሎ በምድብ ስምንት በተደረገ ጨዋታ ፖርቹጋል ጋናን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ የፖርቹጋልን የመጀመሪያ ግብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በፍጹም ቅጣት ምት በ65 ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡ ጃኦ ፍሊክስ እና ራፋይል ሌዮ ደግሞ 78 ኛው እና 80ኛው ደቂቃ ላይ የፖርቹጋልን…