ስፓርት
የዓለም የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድርን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ሪከርድ በመስበር አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርን በሪሁ አረጋዊና እጅጋየሁ ታዬ ሪከርድ በመስበር ጭምር አሸነፉ፡፡
በፈረንጆቹ የ2021 የመጨረሻዋ ቀን በስፔን ባርሴሎና በተደረገ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውያኑ ሪከርድ ሰብረው ማሸነፋቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሪሁ ውድድሩን በ12:49 በሆነ ሰዓት እንዲሁም፥ እጅጋየሁ በ14:19 በሆነ ሰዓት የርቀቱን የዓለም ሪከርድን ጭምር በማሻሻል ነው…
Read More...
ዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ሱዳንን አሸነፉ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወዳጅነት ጨዋታ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን ድል ቀንቶታል።
በካሜሩን ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ማምሻውን ከሱዳን አቻው ጋር የአቋም መለኪያ የወዳጅነት ጨዋታ አድርጓል።
ጨዋታውን ዋልያዎቹ 3 ለ 2 ያሸነፉ ሲሆን፥ የድል ጎሎቹን አማኑኤል ገብረሚካኤል…
አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓመቱ 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን ውስጥ ተካተተች
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኒው አፍሪካ መፅሔት በፈረንጆቹ 2021 ተፅዕኖ ፈጣሪ ነበሩ ካላቸው 100 አፍሪካውያን ዝርዝር ውስጥ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ተካተተች፡፡
በስፖርቱ ዘርፍ ከተመረጡ ተፅጽኖ ፈጣሪዎች መካከል ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ቀዳሚ ስትሆን÷ መፅሔቱ የለተሰንበትን የተፅዕኖ ፈጣሪነት ታሪክ ሲጀምር ክብረ ወሰኖችን…
የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌደሬሽን 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌደሬሽን ዛሬ ባከናወነው 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ጉባዔውን የመሩት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ፍትህ ወልደ ሰንበት (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የዞን አምስት እጅ ኳስ ሻምፒዮና እንድታዘጋጅ ብትመረጥም ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ውድድር ለማከናወን አመቺ አይደለም…
ኬሊያን ምባፔ በጥር ዝዉዉር መስኮት ፒ ኤስ ጅን እንደማይለቅ አስታወቀ
አዲስ አበባ ታህሳስ 20፣ 2014(ኤፍ ቢሲ) ፈረንሳዊዉ ኮከብ ኬሊያን ምባፔ በጥር ዝዉዉር መስኮት ፒ ኤስ ጅን እንደማይለቅ እና ከክለቡ ጋር ተጨማሪ ዋንጫዎችን ማንሳት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡
ተጫዋቹ በጥር የዝውውር መስኮት ሪያል ማድሪድን ይቀላቀላል በሚል የሚወጡ መረጃዎችን አስመልክቶ በሰጠዉ ምላሽ፥ በጥር ወር ክለቡን የመልቀቅ እቅድ እንደሌለዉ እና ከክለቡ ጋር…
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ካሜሩን ለሚያደርገው ጉዞ የሽኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 16፣2014 (ኤፍ ቢሲ)የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ካሜሩን ለሚያደርገው ጉዞ በስካይ ላይት ሆቴል የተሰናዳው የሽኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
ዋልያዎቹ በሀገር ባህል ልብስ አሸብርቀው በስፍራው የተገኙ ሲሆን፥ የመንግሥት ባለስልጣናት ፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዝግጅቱ ላይ መታደማቸዉን ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን…
ሀዋሳ ላይ ሲደረግ የነበረው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ዘጠኝ የጨዋታ ሳምንታትን ያስተናገደው የሃዋሳ ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ዛሬ ከሚደረጉ ጨዋታዎች ባህር ዳር ከነማ ከአዳማ ከነማ ጋር 9፡00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የቀድሞው የባህር ዳር ከነማ አሰልጣኝ ፋሲል…