Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉ 25 ተጫዋቾች ዝርዝር ታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉት 25 ተጫዋቾችን ይፋ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ አህጉራዊ ውድድር መመለሱ ይታወቃል። ዋልያዎቹ በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ አንድ ከአስተናጋጇ ካሜሩን፣ ኬፕ ቨርዴ እና ቡርኪና ፋሶ ጋር መደልደላቸው ይታወሳል። በዚህ መሰረት፤ ግብ ጠባቂዎች፤ ፋሲል ገ/ሚካኤል ተ/ማርያም ሻንቆ ጀማል ጣሰው ተከላካዮች፤ አስቻለው ታመነ ያሬድ ባየ ምኞት ደበበ መናፍ አዎል…
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ሃዲያ ሆሳዕና ሲዳማ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን 2 ለ 0 አሸንፎታል። ምሽት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና በሃዲያ ሆሳዕና 1 ለ 0 ተሸንፏል።

በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የጎዳናና የአገር አቋራጭ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በታይዋን በተደረገ የታይፒ ማራቶን ውድድር በወንዶች ደመቀ ካሰው 2 ሰአት ከ11 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ መሰረት…

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል። ዛሬ በተካሄዱት ሁለት ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስንና ወላይታ ዲቻን ባገናኘው የመጀመሪያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በተደረገ…

በስፔን እና በሜክሲኮ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት በተደረጉ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በስፔን በተደረገ የማላጋ ማራቶን ውድድር በሴቶች÷ አትሌት ፅግነሽ መኮንን አንደኛ፣ ያይንአበባ እጅጉ ሁለተኛ እንዲሁም ማሪቱ ከተማ አምስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡ በሜክሲኮ…

የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 350 ሺህ ዶላር መደበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሽብር ቡድኑ ህወሃት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 350 ሺህ ዶላር መመደቡን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አስታወቁ፡፡ በዚህም 100 ሺህ ዶላሩን ወዲያውኑ ቀሪውን ደግሞ በ5 ዓመት ለመላክ ወስኗል ነው ያሉት አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው::…

በፕሪሚየር ሊጉ ባህር ዳር ከተማ እና ሃዲያ ሆሳዕና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል። ዛሬ በተካሄዱት ሁለት ጨዋታዎች ባህር ዳር ከተማ እና ሃዲያ ሆሳዕና ድል ቀንቷቸዋል። ባህር ዳር ከተማን ከወላይታ ዲቻ ባገናኘው ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ 3 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሃዲያ ሆሳዕና መከላከያን 2 ለ 0…