ስፓርት
ፈረሰኞቹ በቻምፒየንስ ሊጉ ቅድመ ማጣሪያ ከሱዳኑ አልሂላል ጋር ይጫወታሉ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሱዳኑ አልሂላል ጋር እንደሚያደርግ ታውቋል።
ዛሬ ካይሮ ላይ በወጣው የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ እጣ አወጣጥ ፕሮግራም መሠረት ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሜዳቸው ያደርጋሉ።
ቡድኑ በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ጨዋታው ከደቡብ ሱዳን ከዛለን እና ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል።
በተያያዘ የ2014 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግን በሁለተኝነት ያጠናቀቀው የፋሲል ከነማ በአፍሪካ…
Read More...
አቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዝውውሩን አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና የዋሊያዎቹ አጥቂ አቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዝውውሩን ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡
አቡበከር ከወራት በፊት ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት ወደ ደቡብ አፍሪካ ቢያቀናም ዝውውሩ በፊፋ ሳይረጋገጥ ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ አጥቂው በዛሬው ዕለት…
ኢትዮጵያ የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን 3ኛ በመሆን አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ የተካሄደውን የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስተኛ በመሆን አጠናቀቀች።
በውድድሩ ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።
በሻምፒዮናው ማጠናቀቂያ እለት አራት ወርቅ እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።
በሻምፒዮናው…
በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።
በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍፃሜ ውድድር የተሳተፈው አትሌት ልኬነህ አዘዘ በ7:44.06 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አምጥቷል።
ሌላው በውድድር የተካፈለው ኢትዮጵያዊ አትሌት ድርባ ግርማ…
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀምራል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከወራት እረፍት በኋላ ዛሬ ይጀመራል፡፡
ሊጉ ዛሬ ሲጀምር ክሪስታል ፓላስ ከአርሴናል ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሼልስት ፓርክ ሰታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በመርሃ ግብሩ የመጀመሪያ ሳምንት በነገው እለት ስድስት ጨዋታዎችን የሚደረጉ ሲሆን ሊቨርፑል ከፉልሃም፣ቼልሲ ከኤቨርተን እንዲሁም…
ኢትዮጵያ በሴቶች የ3ሺህ ሜትር መሠናክል ውድድር ብርና ነሐስ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች የ3ሺህ ሜትር የመሠናክል ውድድር ኢትዮጵያ ብር እና ነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች፡፡
ሌሊት ላይ በተካሄደ የፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ሲንቦ ዓለማየሁ 9 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ሁለተኛ በመውጣት…
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገበው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የማበረታቻና የእውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የማበረታቻና የእውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ማምሻውን ባዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፥…