ስፓርት
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም ግማሽ ማራቶን ሪከርድን ሰበረች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ዛሬ በተደረገው የቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ውድድር የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች፡፡
አትሌቷ 1 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ በመግባት ነው አሸናፊ
የሆነችው፡፡
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡
ምንጭ፡-World Athletics
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- …
Read More...
የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር መር ሃ ግብር ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት /ሴካፋ/ የ2021 ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር በስድስት ሀገራት መካከል እንደሚደረግ የውድድሩ አዘጋጀች አሳውቀዋል፡፡
ከጥቅምት 20 እስከ ጥቅምት 30 / 2014 ዓ.ም በዩጋንዳ በሚካሄደው ውድድር ላይ ስድስት ሀገራት በዙር መልኩ…
ዋልያወቹ ከጋና የሚያደርጉት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በኦርላዶ ስታዲየም ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና የጋና የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ ኦርላዶ ስታዲየም እንዲካሄድ ኢትዮጵያ መምረጧን የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ገለፀ::
የባሕር ዳር ስታዲየም በካፍ ከታገደ በኋላ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሀገር ውጭ…
በፊፋ ወርሃዊ የሃገራት ደረጃ ኢትዮጵያ ሶስት ደረጃዎችን ወርዳለች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፊፋ ወርሀዊ የዓለም ሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሶስት ደረጃዎችን ወደ ታች ወርዷል፡፡
በወሩ ዋልያዎቹ ባለፈው መስከረም ወር ከነበረበት ደረጃ ዝቅ በማለት በ137ኛ ደረጃ ተቀምጧል።
በተያያዘም በሴቶች ወርሀዊ የደረጃ ሰንጠረዥ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ112ኛ ደረጃ ይገኛል።…
በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ሃድያ ሆሳዕናን 3 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃዋሳ ላይ በተደረገዉ የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ሃድያ ሆሳዕናን 3 ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የፋሲል ከነማን 3 የማሸነፊያ ግቦች ፈቃዱ አለሙ ሲያስቆጥር÷ የሃዲያ ሆሳዕናን ብቸኛ ግብ ደግሞ ባዬ ገዛኸኝ አስቆጥሯል፡፡
በተያያዘም ፋሲል ከነማ የ2013…
አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የ”ኢምፓክት አዋርድ” ተሸላሚ ሆነች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በአሜሪካ የሚገኘው ኖቫ ኮኔክሽንስ የሚያዘጋጀው "ኢምፓክት አዋርድ" ተሸላሚ ሆነች።
አትሌቷ በአትሌቲክስ ዘርፍ በተደጋጋሚ ባስመዘገበቻቸው አስደናቂ ውጤቶች እና በዓለም ላይ ለሚገኙ ታዳጊዎች ትልቅ የስኬት ተምሳሌት በመሆኗ ነው ተሸላሚ የሆነችው ተብሏል።
ሌላው ተሸላሚ አቶ በረከት ወልዱ በዋሽንግተን…
የ2014 ቤትኪንግ ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀምራል።
በዛሬው የመክፈቻ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ ከጅማ አባጅፋር 8 ሰዓት ጨዋታቸውን ሲያደርጉ÷ ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ዲቻ ደግሞ 12 ሰዓት ይጫወታሉ፡፡
ፎቶ፡-ሶከር ኢትዮጵያ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ…