ስፓርት
አስቶንቪላ ስቲቨን ጄራርድን አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ አስቶንቪላ ዲን ስሚዝን ካባረሩ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ ለማግኘት ፍለጋ ላይ ቆይተዋል።
በዛሬው እለትም የቀድሞውን የሊቨርፑል አማካይ ስቲቨን ጄራርድ አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡
የስኮትላንዱ ክለብ ሬንጀርስ አሰልጣኝ የነበረው ጄራርድ አስቶንቪላን በሁለት አመት ተኩል ኮንትራት በአሰልጣኝነት ተረክቧል።
የ41 አመቱ እንግሊዛዊ እና የቀድሞው የሊቨርፑል ኮከብ በሬንጀርስ ቆይታው ከቡድኑ ጋር የስኮቲሽ ፕሪሚየር ሊግን ዋንጫ ማንሳቱ የሚታወስ ነው፡፡…
Read More...
ኢትዮጵያ የሴካፋ ውድድር ሻምፒዮን ሆነች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዙሩ ካደረጋቸው 4 ጨዋታዎች ሁሉንም በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ሻምፒዮን ሆነ ።
ብሄራዊ ቡድኑ 12 ነጥብ በመያዝ 12 ነጥብ ካለው ዩጋንዳ አቻው ጋር የመጨረሻውን የዋንጫ ጨዋታ በዛሬው ዕለት ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ባደረገው ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው…
አትሌት ዳዊት ስዩም የ5 ኪሎ ሜትር ሚክስድ ሬስ የዓለም ሪከርድ ሰበረች
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ)በፈረንሳይ ሊል በተደረገ የ5 ኪሎ ሜትር የድብልቅ ውድድር (ሚክስ ሬስ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዳዊት ስዩም የርቀቱን የዓለም ሪከርድ በመስበር አሸንፋለች።
አትሌቷ በ14:41 በመግባት ነው የርቀቱን የዓለም ሪከርድ በመስበር አሸናፊ መሆን የቻለችው፡፡
በተጨማሪም አትሌት መስከረም ማሞ በ14:55 በሆነ ሰዓት 3ኛ ደረጃ ይዛ…
ኢትዮጵያ ጂቡቲን 7 ለ 0 ረታች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ውድድር ኢትዮጵያን ከጂቡቲ ባገናኘው መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ድል ቀንቷታል፡፡
በዚሁ መሠረትም ኢትዮጵያ የጂቡቲ አቻዋን 7 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡
ጎሎቹንም÷ ረድዔት አስረሣኸኝ 3፣ ቱሪስት ለማ 2፣ ዕፀገነት ግርማ እና ቤተልሔም በቀለ…
ሉሲዎቹም ከ2022 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ውጪ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያ ዙር ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዩጋንዳን 2 ለ0 ማሸነፍ ብትችልም በድምር ውጤት ሉሲዎቹም ከ2022 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ውጪ ሆነዋል።
ኢትዮጵያና ዩጋንዳን በድምር ውጤት 2 እኩል መሆናቸውን ተከትሎ በተሰጠ የመለያ ምት ዩጋንዳ 2 ለ1 በማሸነፏ ሉሲዎቹ ከ2022 የአፍሪካ…
ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዮገን የ2014 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ ሆነች
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕየጎን የ2014 ቶታል ኢነርጂ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ እንደምትሆን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታወቀ።
አትሌት ፌዝ ኪፕየጎን በ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር በሪዮ እና ቶኪዮ ኦሊምፒክ አሸናፊ መሆኗ ይታወቃል።
2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ ህዳር 5 ቀን 2014 ዓ.ም…
የቤጂንግ ማራቶን በኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ስርጭት ሳቢያ ተራዘመ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤጂንግ ማራቶን ውድድር የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ስርጭት በሀገሪቱ በፈጠረው ስጋት ምክንያትለሌላ ጊዜ መራዘሙን የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡
ቻይና ኮቪድ-19 በሀገሪቱ ለሚካሄደው ማራቶን ውድድሩ ስጋት እንዳይሆን እና የሥርጭት ሂደቱን ለማስወገድ በርካት ስራዎች ስትሰራ መቆየቷ ተመላክቷል፡፡…