Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜው ውድድር አለፉ። በርቀቱ ኢትዮጵያን ወክለው ከተካፈሉት አትሌቶች ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይ እና ዳዊት ስዩም ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል በወንዶች 800 ሜትር ማጣሪያ ቶለሳ ቦደና ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል።
Read More...

ኢትዮጵያ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ፍፃሜ በሁለት አትሌቶች ትወከላለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንጋቱ 11 ሰዓት ከ45 ላይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል፡፡ በፍጻሜው መቅደስ አበበ እና ወርቅውሃ ጌታቸው ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። በሌላ በኩል ከሌሊቱ 8 ሰዓት ከ25 ላይ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች የማጣሪያ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን÷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣…

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ 2ኛ ላይ ተቀምጣለች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሬጎን እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ 2ኛ ስፍራን ይዛለች፡፡   በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ እስካሁን ሶስት የወርቅ እና ሶስት የብር ሜዳሊያ በማምጣት ነው ከአሜሪካ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው፡፡   በሴቶች 10 ሺህ ሜትር…

ንጋት ላይ በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያ ሁለት የብር ሚዳሊያዎች አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች በ1 ሺህ 500 ሜትር ፍፃሜ በጉዳፍ ፀጋይ ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የብር ሜዳልያ አገኘች። በውድድሩ ኬንያ የወርቅ እና ብሪታኒያ የነሃስ ሜዳሊያ አገኝተዋል። በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል። አትሌት ለሜቻ…

አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ 3ኛውን የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች። ከሰአት በኋላ በተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቃለች። ርቀቱን 2 ሰአት ከ18 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመግባት ነው…

የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በለተሰንበት ግደይ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በለተሰንበት ግደይ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደረገ። በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች በመጨረሻዎቹ ሰከንዶች ለተሰንበት ግደይ ሄለን ኦቢሪን በክርን መታታለች በሚል ኬንያ ለዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቅሬታ አስገብቷል፡፡ ይሁን እንጅ ለተሰንበት ሄለንን በውድድሩ ፍፃሜ አካባቢ…

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሦስት የፍጻሜ ውድድሮች ትሳተፋለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ኢትዮጵያ በሦስት የፍጻሜ ውድድሮች ትሳተፋለች፡፡ በዚህም መሰረት ቀን 10:15 በሚካሄደው የሴቶች ማራቶን ፍጻሜ ጎይቲቶም ገብረስላሴ፣ አባበል የሻነህ እና አሸቴ በከሪ ይሳተፋሉ፡፡ ሌሊት 11፡20 በሚካሄደው የወንዶች 3 ሺህ…