Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በቤልጂየም የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት ምሽት በቤልጂየም በተካሄደው የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ መዲና ኢሳ ርቀቱን በ15 ደቂቃ14 ሰከንድ በ01 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ በቀዳሚነት አጠናቃለች፡፡ ሌላኛዋ አትሌት አሳየች አይቸው ደግሞ ርቀቱን በ15 ደቂቃ በ14 ሰከንድ በ77ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌደረሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሐዋሳ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሐዋሳ ከተማ ድል ቀንቶታል። ረፋድ ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ መከላከያን 2 ለ 1 አሸንፏል። መከላከያ በተሾመ በላቸው ጎል ጨዋታውን መምራት ቢችልም፥ ሐዋሳ ከተማ በብሩክ በየነ እና ወንድአገኝ ሐይሉ ጎሎች 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል። ከሰአት በኋላ በተካሄደ ሁለተኛ ጨዋታ…

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 በማሸነፍ ለዋንጫ የሚያደርገውን ፉክክር አጠናክሯል፡፡ ምሳ ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ሙጅብ ቃሲም ለፋሲል ከነማ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሱራፌል ዳኛቸው ቀሪዋን አንድ ጎል በፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል፡፡…

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ጅማ አባጅፋርን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሣምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ረፋድ ላይ በተካሄደ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የወልቂጤ ከተማን የአሸናፊነት ጎሎች÷ ዋህብ አዳምስ፣ በኃይሉ ተሻገር እና ጫላ ተሸታ አስቆጥረዋል፡፡ ክትፎዎቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ÷ ነጥባቸውን 35 በማድረስ ከሀዲያ…

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር  ሊግ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ዲቻ ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ረፋድ ላይ በተደረገው ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር በመሱድ መሀመድ ጎል እስከ እረፍት መምራት ቢችሉም ከረፍት መልስ አበባየሁ አጂሶ ባሰቆጠሯቸው ጎሎች ወላይታ ዲቻ ሙሉ 3 ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡ የጦና ንቦች…

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባህርዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ28ኛ ሳምንት በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባህርዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ጨዋታውን ላደረገው ባህርዳር ከተማ መናፍ አወል ብቸኛዋ የማሸነፊያ ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡ የጣና ሞገዶቹ ዘሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 33 በማድረስ ከወራጅ ቀጠና ሸሽተዋል፡፡…