Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን የዓለም ክብረወሰን ሰበረች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትውልድ ኢትዮጵያዊቷ በዜግነት ሆላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን በ10ሺህ ሜትር ሴቶች አዲስ የዓለም ክብረወሰን ሰበረች :: አትሌቷ በጀረንጆቹ 2016 በኢትዮዽያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ተይዞ የነበረውን ርቀት በማሻሻል ነው አዲስ የዓለም ክብረወሰን የሰበረችው፡፡ በዚህም በ2016 በአትሌት አልማዝ አያና በ29 ደቂቃ 17 ሰከንድ በ45 ማይክሮ ሰከንድ ተይዞ የነበረውን ርቀት ዛሬ በኔዘርላንድ ሄንጌሎ በተካሄደው ውድድር በ 29 ደቂቃ 6 ሰከንድ 82 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት…
Read More...

ለሴካፋ ውድድር ዝግጅት ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ተጫዋቾች ጥሪ  ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ዝግጅት ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ። ከ23 ዓመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት የእግርኳስ ውድድር ከሰኔ 26፣2013 እስከ ሐምሌ 11፣2013ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል።…

በሀረሪ ክልል “ስለ አባይ እሮጣለሁ”  የጎዳና ላይ የሩጫ  ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀረር ከተማ ከጨለንቆ  አደባባይ  እስከ ራስ  መኮንን  አደባባይ  "ስለ አባይ እሮጣለሁ" የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ፡፡ የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትና  የክልሉ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በጋራ ያዘጋጁት  ውድድር ነው። በውድድሩ…

ፋሲል ከነማ ከሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት አደረገ። በስምምነቱ መሰረት ሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ለፋሲል ከነማ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የመጫዎቻ ጫማ፣ ኳስ፣ ማሊያዎችና የማሰልጠኛ ቁሳቁሶች በድጋፍ መልክ እንደሚሰጥ ከክለቡ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።…

ፋሲል ከነማን በገቢ ለማጠናከር ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በጎንደር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ማእድ የንጉስ እራት በሚል ክለቡን በገቢ ለማጠናከር ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት ቅጥር ግቢ ዛሬ ምሽቱን ተካሂዷል፡፡ በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአማራ ክልላዊ መንግስትርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ÷ ለፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ክለብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል…

ሶስቱ የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በ2014 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሶስቱ የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በ2014 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አሳወቁ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ግንቦት 24ቀን 2013ዓ.ም ከ3ቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ጋር ስለ ቀጣይ የውድድር ዘመን ተሳትፏቸው በተመለከተ ውይይት…

የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ቡድንና ዳሽን ቢራ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ቡድንና ዳሽን ቢራ የአምስት ዓመት የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አቶ ድረስ ሳህሉና የዳሽን ቢራ የንግድ ክፍል ዳይሬክተር ፓትሪክ ተፈራርመዋል፡፡ በተደረገው ስምምነት መሰረት ባህርዳር ከተማ…