Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ዓመት መራዘሙን ዓለም ዓቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ በአውስትራሊያዋ ባትረስት ከተማ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በየካቲት 19/2022 ሊያካሄደው አቅዶት የነበረውን 44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአንድ ዓመት ማራዘሙን ገልጿል፡፡ ሻምፒዮናው የተራዘመበት ምክንያትም አውስትራሊያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከለከል ከመላው ዓለም…
Read More...

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ውጤት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የ2021 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ተጀምሯል፡፡ ከምድብ 5 እስከ 8 የሚገኙ ቡድኖች የመጀመሪያ ዙር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ አከናውነዋል፡፡ ምሽት በተካሄደው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ ሲሸነፍ ቼልሲ ድል ቀንቶታል፡፡  የጨዋታዎች ዝርዝር ውጤትም÷…

ፋሲል ከነማ ከአል ሂላል ጋር አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ ጨዋታ ከአል ሂላል ጋር አቻ ሲለያይ ኢትዮጵያ ቡና በዩ አር ኤ ሽንፈት ገጥሞታል። የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ ባህርዳር አለማቀፍ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡ በጨዋታው ፋሲል ከነማ ከአል ሂላል ጋር 2 አቻ ተለያይቷል፡፡ በሌላ በኩል ለካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ…

አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በ5 ኪ. ሜ የሩጫ ውድድር የአለም ሪከርድ ሰበረች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ የአለም ሪከርድ ሰብራለች፡፡ አትሌቷ በሄርዞጌናውራች በተካሄደው የ‘አዲዜሮ ሮድ ቱ ሪከርድስ’ ውድድር ነው 14 ደቂቃ ከ 21 ሰከንድ በመግባት ሪከርዱን የሰበረችው፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ የሴካፋ ውድድርን 2ተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬኒያ ናይሮቢ ሲካሄድ በሰነበተው የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና (ሴካፋ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በኬኒያ አቻው ተሸንፎ 2ተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ዛሬ ከቀኑ 10፡00 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ከኬኒያው ቬጋ ኩዊንስ ጋር ባደረገው…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ዛሬ የፍጻሜ ጨዋታውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይሮቢ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና (ሴካፋ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የፍጻሜ ጨዋታውን ዛሬ ያካሂዳል፡፡ በግማሽ ፍጻሜው የኡጋንዳውን ሌዲ ዶቭስን በመለያ ምት በአጠቃላይ ውጤት 6 ለ 4 በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሱ ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሠረት…

የኢትዮጵያ ቮሊቦል ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ሱዳን አቻውን 3 ለ 2 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የወንዶች ቮሊቦል ሻምፒዮና ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቮሊቦል ብሔራዊ ቡድን ደቡብ ሱዳን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል ። ከነሀሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሩዋንዳ ኪጋሊ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ የወንዶች ቮሊቦል ሻምፒዮና እስከ መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ.ም…