Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባ ጅፋርን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባ ጅፋርን 3 ለ 2 አሸንፏል። ጌታነህ ከበደ የቅዱስ ጊዮርጊስን ሶስቱን የድል ጎሎች በማስቆጠር ሐት ትሪክ ሰርቷል። የጅማ አባ ጅፋርን ጎል ደግሞ ሮባ ወርቁና ቤካም አብዱላ አስቆጥረዋል፡፡ ከቀትር በኋላ 9 ሰአት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ወላይታ ዲቻ ከሰበታ ከተማ ያለምንም ጎል አቻ በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡ ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ…
Read More...

 የአዲስ አበባ ስታዲየምን የዕድሳት ስራ ለማከናወን ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ስታዲየምን የዕድሳት ስራ ለማከናወን ስምምነት  መፈረሙን የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ። ስምምነቱ የተፈረመው የዲዛይን ፣ የማማከርና የቁጥጥር አገልግሎቱን ከሚያከናውነው ዮናስ አባይ አማካሪ አርክቴክቸር እና ኢንጅነሪንግ ከተባለ ድርጅት ጋር ነው። የዲዛይን ስራውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ…

ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት 28 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበላቸው

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከሁለት ወራት በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጅማ ለሚያርደርገው ዝጅግት 28 ተጫዋቾች ተጠርተዋል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ባደረጉት ጥሪ አመዛኞቹ ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም ከኒጀር ባደረጉት ጨዋታ የተጠቀሙባቸው ሲሆኑ ጥሩ አቋም ላይ የሚገኙት ፍሬው ጌታሁን፣ ፋሲል ገብረሚካኤል፣ ኤልያስ…

ሊዲያ ታፈሰ ብቸኛዋ ሴት የመሀል ዳኛ በመሆን የወንዶችን የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ትመራለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሮን አዘጋጅነት የሚካሄደው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የሚመሩ ዳኞችን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ኮሚቴ ከ31 ሀገራት 47 ዋና ዳኞች ፣ ረዳት ዳኞች እና የቪዲዮ ረዳት ዳኞችን መርጧል። በዚህም ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ የቻን የአፍሪካ ዋንጫ በዋና ዳኝነት የምትመራ…

የ2013 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 ታላቁ ሩጫ ሁሉንም የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል እና መከላከያ መንገዶች ተከትሎ መካሄዱ ተገልጿል። ውድድሩ መነሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ ሲሆን መድረሻው ደግሞ አትላስ አካባቢ መሆኑ ታውቋል፡፡ በውድድሩ ከጤና ሯጮች በተጨማሪ 300 የሚሆኑ ወንድ እና ሴት አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡…

3ኛው ዙር የከተማ አቀፍ የሰላም ንቅናቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው ዙር የከተማ አቀፍ የሰላም ንቅናቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሄደ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴው አምቼ መነሻውን አድርጎ ወደ ቦሌ በሚወስደው የቀለበት መንገድ ላይ ተካሂዷል። ሶስተኛው ዙር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ "ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ…

ወላይታ ዲቻ ዋና አስልጣኙን ደለለኝ ደቻሳን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ዋና አስልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ እና ምክትል አሰልጣኙን ማሰናበቱን አስታወቀ፡፡   የወላይታ ዲቻ የስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ፎላ በክለቡ ወቅታዊ አቋም ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።   አቶ ሳሙኤል ከስድስት ጨዋታዎች አንድ ብቻ በማሸነፉ በዋና እና በምክትል አሰልጣኝ…