Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል። ረፋድ ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 3 ለ 1 አሽንፏል። ታፈሰ ሰለሞን፣ አቡበክር ናስር እና ሃብታሙ ታደሰ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል። በዛብህ መለዮ ደግሞ የፋሲል ከነማን የማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል። ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና…
Read More...

የብሔራዊ ስታዲየም የጣራ መሸከሚያ ምሰሶ ኮንክሪት ሙሌት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ስታዲየም የጣራ መሸከሚያ ምሰሶ ኮንክሪት ሙሌት ተጀመረ። የስታዲየሙ ሁለተኛው እና የማጠቃለያ ምዕራፍ ግንባታ የፊርማ ስነ ስርአት በዛሬው እለት ተካሄዷል፡፡ በዚህ ወቅትም የፕሮጀክቱ የሁለተኛ ምዕራፍ ስራው ዋና አካል የሆነው የጣራ መሸከሚያ ምሰሶ ኮንክሪት ሙሌት ስራ ተጀምሯል፡፡ በኮንክሪት ሙሌት…

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በኡጋንዳ አቻው ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በኡጋንዳ አቻው ተሸነፈ፡፡ የኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ አንድ ግብ በማስቆጠር ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸነፈው፡፡ በምድብ ኤ  ኢትዮጵያ ኡጋንዳን በመከተል ወደ…

በፕሪሚየር ሊጉ ሰበታ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ተካሄዷል፡፡ ረፋድ ላይ ሃዋሳ ከተማ ከተማን ከሰበታ ከተማ ባገናኘው ጨዋታ ሰበታ ከተማ ድል ቀንቶታል፡፡ ጨዋታውን ሰበታ 3 ለ 1 ሲያሸንፍ አለማየሁ ሙለታ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ እና ፉአድ ፈረጃ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡ መስፍን ታፈሰ ደግሞ ለሃዋሳ…

ኢትዮጵያ ያስተናገደችዉ የአኖካ ጉባኤ ዝግጅት ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያስተናገደችዉ የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ጉባኤ ዝግጅት ስኬታማ እንደነበር ተገለፀ፡፡ የአኖካ ጉባኤ እና የጠቅላይ ሚኒስትር አዐይ አሕመድ የሽልማት እና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄዷል፡፡ በመርሃ ግብሩ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ፣ የዉጭ…

ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በወንዶች የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖላንዳዊው አጥቂ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በወንዶች የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ሽልማትን አሸነፈ፡፡ ሌዋንዶውስኪ ባለፈው የውድድር አመት ከክለቡ ባየርን ሙኒክ ጋር ስኬታማ የውድድር አመት ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ አጥቂው ከክለቡ ጋር የሶስት ዋንጫዎች ባለቤት ሲሆን፥ በ47 ጨዋታዎችም 55 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ በጀርመን…

የወላይታ ቱሳ ስፖርት ክለብ መስራች አባ ጂኖ ቤናንቲ አረፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013(ኤፍቢሲ) የወላይታ ቱሳ ስፖርት ክለብ መስራች አባ ጂኖ ቤናንቲ አረፉ። ጣሊያናዊው አባ ጂኖ ቤናንቲ በጣሊያን ሀገር ሳን ሰቨሪኖ ደልማርክ በምትባል ምዕራብ ጣሊያን ከተማ እ.አ.አ. ሚያዝያ 23 ቀን 1944 ተወልደው በካቶሊክ ቤተ እምነት ሚሲዮናዊ ሆነው እ.አ.አ በወርሃ ሰኔ 1963 ዓ.ም የዛሬ 50 አመት ወደ ኢትዮጵያ በተለይም በወላይታ…