ስፓርት
በአዲስ አበባ የሚገኙ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ለ20 ሺህ ተማሪዎች ጫማ ለመለገስ ቃል ገቡ
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 27 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ለ20 ሺህ ተማሪዎች ጫማ ለመለገስ ቃል ገብተዋል።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት 'አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ' በሚል ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ እና ቃልኪዳን ማስገቢያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዋል።
የስፖርት ቤተሰቡ በእለቱ ብቻ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት 20 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን ጫማ ለማጨመት ቃል ገብተዋል፡፡
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመርሃ ግብሩ ላይ÷የከተማ አስተዳደሩ ላቀረበው…
Read More...
ቼልሲ ቲያጎ ሲልቫን አስፈረመ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫ የእንግሊዙን ቼልሲ ተቀላቀለ፡፡
ሲልቫ ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ የማራዘም አማራጭ ያለው የአንድ አመት የኮንትራት ፊርማውን አኑሯል፡፡
የ35 አመቱ ተከላካይ ሰማያዊዎቹን በነጻ ዝውውር ከፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ ተቀላቅሏል፡፡
ሲልቫ በዘንድሮው ክረምት የቼልሲ አራተኛው ፈራሚ ሆኗል፡፡…
ባየር ሙኒክ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ለ6ኛ ጊዜ አነሳ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጀርመኑ ባየር ሙኒክ የፈረንሳዩን ፓሪስ ሴንት ጀርመንን በመርታት ቻምፒየንስ ሊጉን ለ6ኛ ጊዜ አንስቷል።
የ2019/2020 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ትናንት ምሽት በፖርቹጋል ዋና ከተማ ሊዝበን ተካሂዷል።
በፍፃሜው የጀርመኑ ባየር ሙኒክ ከፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርመን የተገናኙ ሲሆን፦ ባየር ሙኒክ…
ሴቪያ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ ትናንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
በጀርመን ኮሎኝ የተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ የስፔኑን ሴቪያ ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ተገናኝተው ሴቪያ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል፡፡
በጨዋታው ኢንተር ሚላን በሮሜሉ ሉካኩ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል ቀዳሚ መሆን ችሎ ነበር፡፡
ይሁን እንጅ ደ ዮንግ…
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሊሸጥ ነው
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩን በቴሌቪዥን ማስተላለፍ ለሚችሉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑ ታውቋል፡፡
በሀገራችን የሚካሄደው የወንዶች እግር ኳስ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በ16 ክለቦች መካከል በሜዳ እና ከሜዳ ውጭ በሚል የውድድር ፎርማት ይካሄዳል፡፡
በመሆኑም የሊጉ ኩባንያ በቀጣይ…
ሮናልድ ኪዩመን ባርሴሎናን በአሰልጣኝነት ተረከበ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፔኑ ባርሴሎና ሮናልድ ኪዩመንን አሰልጣኙ አድርጎ ሾሟል፡፡
የካታላኑ ክለብ የቀድሞ አሰልጣኙ ኪኬ ሴቲዬንን ከቻምፒየንስ ሊጉ ሽንፈት በኋላ አሰናበቷል፡፡
ይህን ተከትሎም የቀድሞው የክለቡን ተጫዋች ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡
ኪዩመን የኔዘርላንድስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ከ16 አመት በኋላ ተሰበረ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ትናንት ማታ በዑጋንዳዊው አትሌት ቼፕቴጌ ተሻሽሏል፡፡
ጆሹዋ ቼፕቴጌ ትናንት ምሽት በሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር የ5 ሺህ ሜትሩን ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንዶች አሻሽሎታል፡፡
አትሌቱ ርቀቱን 12 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ከ36 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ…