ስፓርት
ዊሊያን በሶስት አመታት ውል አርሰናልን ተቀላቀለ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው የመስመር አማካር ዊሊያን የሰሜን ለንደኑን የእግር ኳስ ክለብ አርሰናልን ተቀላቀለ፡፡
ዊሊያን የምዕራብ ለንደኑን እግር ኳስ ክለብ ቼልሲን በመልቀቅ ወደ አርሰናል በነጻ ዝውውር አምርቷል፡፡
የ32 አመቱ ዊሊያን በአርሰናል ለሶስት አመታት ለመቆየት መስማማቱም ነው የተነገረው፡፡
ዊሊያን በፈረንጆቹ 2013 ከሩሲያው አንዚ ማካቻካላ በ30 ሚሊየን ፓውንድ መፈረሙ ይታወሳል፡፡
ከዚያን ጊዜ ወዲህም ለክለቡ በ339 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡
በቼልሲ የነበረው ስምምነት…
Read More...
በቻምፒየንስ ሊጉ አር ቢ ሌፕዚግ የግማሽ ፍጻሜተፋላሚ መሆኑን አረጋገጠ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ተካሄዷል፡፡
አር ቢ ሌፕዚግ እና አትሌቲኮ ማድሪድን ባገናኘው ጨዋታ የጀርመኑ ክለብ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
በፖርቹጋል ሊዝበን በተደረገው በዚህ ጨዋታ አር ቢ ሌፕዚግ ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ኦልሞ እና አዳምስ ለአርቢ…
በዩሮፓ ሊግ ሲቪያ እና ሻካታር ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተካሄደዋል፡፡
በጀርመን እየተደረገ ባለው ውድድር የስፔኑ ሲቪያ እና የዩክሬኑ ሻካታር ዶኔስክ ግማሽ ፍጻሜ መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ከእንግሊዙ ወልቨርሃምፕተን ወንደረርስ ጋር የተጫወተው ሲቪያ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በጨዋታው ወልቭሶች አዳማ ትራኦሬ…
በዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚዎች ተለይተዋል
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚዎች ተለይተዋል፡፡
ከትናንት በስቲያ እና ትናንት በተደረጉ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች በሩብ ፍጻሜ የሚጫወቱ 8 ቡድኖች ታውቀዋል፡፡
የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎቹ የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
ሰኞ ማንቼስተር ዩናይትድ ከዴንማርኩ ኮፐንሃገን እንዲሁም የጣሊያኑ ኢንተርሚላን…
የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 23 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ ፡፡
ስምምነቱ የተፈረመው የኢትዮጲያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስፖርት ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ጋር ሲሆን÷…
የ2013 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚካሄድበት ጊዜ ተራዘመ
አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 21 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህዳር 6 ቀን ሊደረግ የነበረው የ2013 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተገልጿል።
ድርጅቱ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ÷ የ2013 ዓ.ም ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በወረረሽኙ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉን ገልጿል።
ወደ ፊት ምዝገባ…