ስፓርት
ሊዲያ ታፈሰ ብቸኛዋ ሴት የመሀል ዳኛ በመሆን የወንዶችን የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ትመራለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሮን አዘጋጅነት የሚካሄደው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የሚመሩ ዳኞችን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ኮሚቴ ከ31 ሀገራት 47 ዋና ዳኞች ፣ ረዳት ዳኞች እና የቪዲዮ ረዳት ዳኞችን መርጧል።
በዚህም ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ የቻን የአፍሪካ ዋንጫ በዋና ዳኝነት የምትመራ ብቸኛዋ ሴት መሆኗን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
በተመሳሳይ ሌላኛው ዓለም አቀፍ ዳኛ በአምላክ ተሰማ በቫር ዳኝነት የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ከሚመሩ ዳኞች መካከል አንዱ ሆኖ ተመርጧል።…
Read More...
የ2013 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 ታላቁ ሩጫ ሁሉንም የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል እና መከላከያ መንገዶች ተከትሎ መካሄዱ ተገልጿል።
ውድድሩ መነሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ ሲሆን መድረሻው ደግሞ አትላስ አካባቢ መሆኑ ታውቋል፡፡
በውድድሩ ከጤና ሯጮች በተጨማሪ 300 የሚሆኑ ወንድ እና ሴት አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡…
3ኛው ዙር የከተማ አቀፍ የሰላም ንቅናቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው ዙር የከተማ አቀፍ የሰላም ንቅናቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴው አምቼ መነሻውን አድርጎ ወደ ቦሌ በሚወስደው የቀለበት መንገድ ላይ ተካሂዷል።
ሶስተኛው ዙር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ "ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ…
ወላይታ ዲቻ ዋና አስልጣኙን ደለለኝ ደቻሳን አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ዋና አስልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ እና ምክትል አሰልጣኙን ማሰናበቱን አስታወቀ፡፡
የወላይታ ዲቻ የስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ፎላ በክለቡ ወቅታዊ አቋም ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
አቶ ሳሙኤል ከስድስት ጨዋታዎች አንድ ብቻ በማሸነፉ በዋና እና በምክትል አሰልጣኝ…
የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር ዝግጅት ተጠናቋል
አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጪው እሁድ ለሚካሄደው የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር የዝግጅት ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ።
የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄዎችን ታሳቢ በማድረግ ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄደው 20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ 12 ሺህ 500 ተሳታፊዎች ብቻ እንደሚኖሩት ታውቋል።
ውድድሩ መነሻውን መስቀል…
ጅማ ለፕሪሚየር ሊጉ ውድድር መሰናዶ አስፈላጊ ዝግጅት ማድረጓን የከተማዋ ከንቲባው አረጋገጡ
አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ምዕራፍ ጅማ ላይ ይካሄዳል።
ይህን ተከትሎም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑን የከተማው ከንቲባ በላኩት ደብዳቤ ማረጋገጣቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ጅማ ከተማ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ከሰባተኛው እስከ 11ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎችን ታዘጋጃለች።
ይህን…