Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ተስፋዬ ኡርጌቾ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው ተስፋዬ ኡርጌቾ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ከሚኖርበት አሜሪካ ለዕረፍት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ተስፋዬ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ህክምና ሲከታተል መቆየቱን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም ለመላው ቤተሰቦቹና ለስፖርት ቤተሰቡ መጽናናት ይመኛል። የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር…
Read More...

የ2012 ሁሉም የሊግ ውድድር መሰረዙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2012 ሁሉም የሊግ ውድድር መሰረዙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዛሬው እለት አስታወቀ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ2012 ሲካሄዱ በነበሩ አጠቃላይ የሊግ ውድድሮች እጣ ፈንታ ላይ በዛሬው እለት በቴሌ ኮንፈረንስ እና በአካል በፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።…

የአርባምንጩ ግብ ጠባቂ ፍሬው ገረመው ህይወቱ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ግብ ጠባቂ ፍሬው ገረመው ህይወቱ አለፈ። ፍሬው ገረመው በድንገት ህይወቱ እንዳለፈ እና እስከ ትናትናው ዕለት ልምምድ ሲሰራ መቆየቱ ነው የተነገረው። ግብ ጠባቂው ከሰሞኑ በጉልበቱ ላይ እጢ ወጥቶበት የነበረ ሲሆን በትናትናው ዕለት ልምምድ ከሰራ በኋላ በጉልበቱ ላይ የወጣውን እጢ…

በኢንተርኔት የታገዘና በቀጥታ ስርጭት የሚሳተፉበት የቨርቿል ሩጫ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 20፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታዋቂ አትሌቶች መሪነት በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን የሚያሳትፍ በኢንተርኔት የታገዘና በቀጥታ ቪዲዮ በመታገዝ የቨርቿል ሩጫ እየተዘጋጀ ነው። ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የታላቁ አፍሪካ ሩጫ አዘጋጅ በላከው መግለጫ÷ በብርቅዬ አትሌቶች መሪነት፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን የሚያሳትፍ የቨርቿል ሩጫ አየተዘጋጀ…

ፊፋ የ150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለአባል ሀገራቱ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)ፊፋ በኮሮና ቫይረስ ተጽዕኖ መቋቋሚያ የሚሆን የ150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለአባል ሀገራቱ ሊያደርግ ነው፡፡ የአለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) አባል ሀገራቱ በኮሮና ቫይረስ ከደረሰባቸው የፋይናንስ ተፅዕኖ እንዲወጡ የ150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ የፊፋ አባል ሀገራት በወረርሺኙ…