Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ወደ ድል ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች መስፍን ታፈሰ (2) እና ኤፍሬም ታምራት (በራሱ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት በኋላ ወደ ድል ተመልሷል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተገናኙት አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ…
Read More...

የቪላን የ30 ዓመት የዋንጫ ጥም የቆረጡት የዩሮፓ ሊግ አለቃ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አስቶን ቪላ ከ30 ዓመታት የዋንጫ ጥበቃ በኋላ ትናንት ምሽት የጀርመኑን ክለብ ፍሬቡርግ በማሸነፍ የዩሮፓ ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬ ላለፉት ዓመታት "የምንፈልገውን የሚያውቅ ምርጥ አሰልጣኝ አግኝተናል" በሚል በቪላ ደጋፊዎች ሲዘመርላቸው ቆይተዋል፡፡ ኡናይ ኢምሬ የአሰልጣኝነት ስራን የጀመሩት…

ገደኛው ቪክቶር ዮከሬሽ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቪክቶር ኢናር ዮከሬሽ የተወለደው በአውሮፓዊቷ ሀገር ስዊዲን በፈረንጆቹ 1998 ነው፡፡ በፈረንጆቹ 2015 በሀገሩ ክለብ ብሮማፖጅካርና የመጀመሪያ ጨዋታውን በማድረግ የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ህይወትን የጀመረው ቪክቶር÷ በብራይተን፣ ኮቨንተሪ ሲቲ እና ስዋንሲ ሲቲ በመሳሰሉ የእንግሊዝ ክለቦች ያልተሳካ ጊዜን አሳልፏል፡፡…

በኤሲሚላን ራሱን ለዓለም ያሳየው አንድሪያ ፒርሎ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጣሊያናዊው የኤሲሚላን የቀድሞ ኮከብ አንድሪያ ፒርሎ ከምንጊዜም ምርጥ የመሐል ሜዳ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው፡፡ በፈረንጆቹ 1979 በዛሬዋ ዕለት የተወለደው አንድሪያ ፒርሎ የእግር ኳስ ሕይወቱን የጀመረው በሀገሩ ክለብ ብሬሺያ ነው፡፡ ከምንጊዜም ታላላቅ የመሐል ሜዳ ተጫዋች መካከል አንዱ የሆነው ፒርሎ በእይታው፣…

ዳኒ ካርቫሃል ከሪያል ማድሪድ ጋር ተለያየ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፔናዊው የቀኝ መስመር የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ዳኒ ካርቫሃል ከሪያል ማድሪድ ጋር ተለያይቷል፡፡ የ34 ዓመቱ ተጫዋች በሪያል ማድሪድ ቆይታው 4 የስፔን ላሊጋ፣ 6 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና 2 የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫዎችን ጨምሮ 27 ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡ በፈረንጆቹ 2013 ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን…

በዓለም የኤምኤምኤ ከባድ ሚዛን ውድድር ካሜሩናዊው ፍራንሲስ ንጋኑ በዝረራ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በተካሄደው በዓለም የድብልቅ ማርሻል አርት (ኤምኤምኤ) ከባድ ሚዛን ውድድር ካሜሩናዊው ፍራንሲስ ንጋኑ ብራዚላዊውን ፍሊፕ ሊንስ በመጀመሪያው ዙር ግጥሚያ በዝረራ አሸንፏል፡፡ ትናንት ምሽት በተካሄደው ውድድር ንጋኑ ከብራዚላዊው የኤምኤምኤ ኮከብ ፍሊፕ ሊንስ ከባድ ፉክክር ቢገጥመውም በሰነዘረው ቡጢ…

ሰንደርላንድ እና ሊድስ ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሰንደርላንድ እና ሊድስ ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ የተካሄደው የሰንደርላንድ እና ኤቨርተን ጨዋታ በሰንደርላንድ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል። በጨዋታው የሰንደር ላንድ ግቦችን ኢንዞ ለፌ፣ ብራያን ብሮቤይ እና ዊልሰን ኢሲዶር…