Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ ከወልቭስ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ወልቭስን ይገጥማል፡፡ ማንቼስተር ዩናይትድ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ሲሆን÷ በሦስቱ አቻ ተለያይቶ በአንዱ ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡ ተጋጣሚው ወልቭስ በበኩሉ በዚህ የውድድር ዓመት አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም፡፡ ዩናይትድ በ22 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ወልቭስ በሁለት ነጥብ የሊጉ መጨረሻ ደረጃ 20ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች…
Read More...

የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን የ2018 የውድድር ዓመት የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ማስጀመሪያ እና የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት አከናውኗል፡፡ የ10ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው ውድድሩ ሚዛን አማን ከተማ ከፌደራል ማረሚያ በሚያደርጉት ጨዋታ ከመጪው ታህሳስ 18 ጀምሮ በተመረጡ ከተሞች የሚደረግ ሲሆን፥ የመጀመሪያው ዙር…

በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ለሚሳተፈው የልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ሽኝት ተደርጎለታል። ‎ ‎4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ከታህሳስ 1 እስከ 10/2018 ዓ.ም በአንጎላ ሉዋንዳ ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) በማሪዮት ሆቴል በተዘጋጀው…

ሀዋሳ ከተማ እና መቻል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ9ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ እና መቻል 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኮሊንስ ኮፊ መቻልን መሪ ማድረግ የቻለ ሲሆን፥ የሀዋሳ ከተማን የአቻነት ግብ ጌታነህ ከበደ ከመረብ አሳርፏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ሀድያ ሆሳዕና ከነገሌ አርሲ በሀዋሳ…

አርሰናል በአስቶን ቪላ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አስቶን ቪላ አርሰናልን 2 ለ 1 አሸንፏል። በሜዳው የሊጉን መሪ አርሰናልን ያስተናገደው አስቶን ቪላ ማቲ ካሽ እና ኢሚሊያኖ ቡዌንዲያ ስቆጠሯቸው ግቦች ድል አድርጓል። የአርሰናልን ብቸኛ ግብ ሊያንድሮ ትሮሳርድ አስቆጥሯል።

የ15ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት 7 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ ቀን 9 ሰዓት 30 ላይ የሊጉ መሪ አርሰናል ወደ ቪላ ፓርክ በማቅናት ከአስቶንቪላ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት መድፈኞቹ በሊጉ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፈው…

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የፊፋ የሰላም ሽልማትን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሽልማቱ የተበረከተላቸው በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ባለው የ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት ላይ ነው፡፡ በዚህ ወቅትም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያን…