ስፓርት
የሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ሁለተኛ ቀን የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡
በዚህ መሰረት ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ የቤልጂዬሙ ክለብ ብሩጅ ከጣልያኑ አታላንታ ጋር ይፋለማሉ፡፡
ምሽት 5 ሰዓት ላይ የስኮትላንዱ ሴልቲክ በሴልቲክ ፓርክ ስታዲየም ከባየርንሙኒክ፣ የሆላንዱ ፌይኑርድ ከኤሲሚላን እንዲሁም ሞናኮ በስታዴ ሉዊስ ሁለተኛ ስታዲየም ከቤኔፊካ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ትላንት ምሽት በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ተጠባቂ…
Read More...
በጥሎ ማለፉ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ሲደርጉ ማንቼስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
በጥሎ ማለፉ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ቀደም ብሎ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ የፈረንሳይ ቡድኖች የሆኑት ብረስት እና ፒኤስጂ ይፋለማሉ፡፡
የማንቼስተር ሲቲ…
ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምሽት 12፡00 ላይ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ።
ለወላይታ ድቻ ፀጋዬ ብርሃኑ 45ኛ ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር ለንግድ ባንክ ደግሞ ኪቲካ ጅማ በ14 ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥሯል።
የወላይታ ድቻው ኬኔዲ ከበደ በ26ኛው ደቂቃ ላይ በሁለት ቢጫ…
ባህርዳር ከተማ ፋሲል ከነማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በተካሄደው የ19ኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ መርሃ ግብር ባህርዳር ከተማ ፋሲል ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ለባህርዳር ከተማ ቸርነት ጉግሳ በ46ኛው እና በ91ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር ለፋሲል ከተማ ደግሞ ጌታነህ ከበደ በ50ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት…
ፊፋ የኮንጎ ሪፐብሊክንና የፓኪስታንን እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች አገደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የኮንጎ ሪፐብሊክን እና የፓኪስታንን እግር ኳስ ፌደሬሽኖች ማገዱ ተሰማ።
የኮንጎ እግር ኳስ ማህበር (ፌኮፉት) ከዓለም አቀፍ እግር ኳስ ውድድሮች የታገደው በተቋሙ ውስጥ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብቷል በሚል መሆኑን ፊፋ አስታውቋል።
ፊፋ ሶስተኛ ወገን ያለው…
አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የግማሽ ማራቶን አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዱባይ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸናፊ ሆናለች።
አትሌት ያለምዘርፍ 1 ስዓት ከ7ደቂቃ ከ09 ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት ማጠናቀቋን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል።
13ኛው የሀዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 13ኛው የሀዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ፡፡
21ኪሎ ሜትር በሸፈነው በዚህ ውድድር በወንዶች አትሌት አስቻለው ብሩ ፣በሴቶች ደግሞ ምህረት ገመዳ አሸንፈዋል።
በውድድሩ ከአዋቂዎች ውድድር በተጨማሪ የ 8 ኪ.ሜ የጤና ሯጮች እና የህፃናት ውድድር…