ስፓርት
የሰሜን ኮሪያው መሪ ሶስት የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በሀገራቸው እንዳይታዩ አገዱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ቶተንሃም ሆትስፐር፣ ዎልቭስ እና ብረንትፎርድ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን እንዳይታዩ ማገዳቸው ተገለፀ፡፡
ኪም ጆንግ ኡን ትዕዛዙን የሰጡት በሶስት ክለቦች የሚጫዎቱ የደቡብ ኮሪያ ተጫዋቾችን የሰሜን ኮሪያ ዜጎች እንዳይመለከቷቸው ለማድረግ ነው ተብላል፡፡
የቶተንሃም አምበል እና አጥቂ ሰን ሁንግ ሚን፣ የዎልቭሱ አማካይ ሀዋንገ ሂ ቻን እና የብረንትፎርዱ ተከላካይ ኪም ጂ ሶ የደቡብ ኮሪያ ዜግነት ያላቸው የፕሪሚየር ሊጉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
የማንቼስተር ዩናይትድ…
Read More...
አትሌት ድርቤ በሊዮን 3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንሳይ ሊዮን በተካሄደው የ3 ሺህ ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ ድል ቀንቷታል።
ድርቤ ርቀቱን በ8 ደቂቃ 39 ሰከንድ ከ49 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡
አትሌቷ ያስመዘገበችው ሰዓት የቦታው ፈጣን ሰዓት ሆኖ መመዘገቡም ተጠቁሟል፡፡
ሌላኛዋ አትሌት የኔዋ ንብረት…
ማንቼስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ማንቼስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በውድድር ዓመቱ ደካማ እንቅስቃሴ እያሳዩ የሚገኙት ቶተንሃሞች እና ማንቼስተር ዩናይትዶች ዛሬ ምሽት 1:30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ወገብ ዝቅ ብለው በ14ኛ…
ማንቼስተር ሲቲ ኒውካስል ዩናይትድን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኒውካስል ዩናይትድን አስተናግዶ 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ለማንቼስተር ሲቲ በጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን የተቀላቀለው ግብጻዊው ኦማር ማርሙሽ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሃትሪክ ሲሰራ ማካቴ…
መድፈኞቹ ሌስተር ሲቲን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ወደ ኪንግ ፓወር ስታዲየም አቅንቶ ሌስተር ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የመድፈኞቹን ሁለቱንም ግቦች ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ስፔናዊው ሚኬል ሜሪኖ አስቆጥሯል፡፡
አርሰናል ድሉን ተከትሎ በደረጃ ሰንጠረዡ ከመሪው ሊቨርፑል ያለውን ልዩነት በ4 ነጥብ በማጥበብ…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በዕለቱ የመጀመሪያ መርሃ ግብር ቀን 9:30 አርሰናል ከሜዳው ውጭ ሌስተር ሲቲን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል።
በርካታ የፊት መስመር ተጫዋቾቻቸውን በጉዳት ያጡት መድፈኞቹ በዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ ለመቆየት የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ…
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ውድድር ዛሬ በፍፃሜ በተደረገ የወንዶች እግር ኳስ ጨዋታ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሶማሌ ክልልን 3 ለ 1 በማሸነፍ የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ሻምፒዮን ሆኗል።
በወላይታ ሶዶ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ምዘና ውድድር…