ስፓርት
ቼልሲ ሮማን አብራሞቪችን ካጣ በኋላ ወደ ስኬት የተመለሰበት ዓመት…
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያዊው ባለሃብት ሮማን አብራሞቪች ቼልሲን ለአሜሪካዊው ባለሃብት ከሸጡ በኋላ ይህ ቡድን በርካታ ተጫዋቾችን በውድ ገንዘብ ወደ ስብስቡ ቢቀላቅልም ስኬታማ ሳይሆን ቆይቷል፡፡
ቼልሲ በአሜሪካዊው ባለሃብት ቶድ ቦህሊ ከተያዘ በኋላ በሊጉም ሆነ በሌሎች ውድድሮች ላይ ስኬታማ ጊዜን ለማሳለፍ ሲቸገር ቆይቷል፡፡ በዚህ የውድድር ዓመት ግን የኮንፍረንስ ሊግ ዋንጫን እና የክለቦች ዓለም ዋንጫን በማሳካት ከስኬታ ጋር መገናኘት ጀምሯል፡፡
በወጣት ተጫዋቾች እየተገነባ የሚገኘው ቡድኑ በ2025 ሁለት…
Read More...
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ወደ ናይጄሪያ አቀና
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ወደ ናይጄሪያ አቡኩታ አቅንቷል።
በፈረንጆቹ ከሐምሌ 16 እስከ 20 ቀን 2025 በናይጄሪያ አቡኩታ ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የአትሌቲክስ ልዑክ ወደ…
ልዩነት ፈጣሪው ኮከብ…
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)ለአንድ ወር ያህል በአሜሪካ ሲካሄድ የቆየው የዓለም ክለቦች ዋንጫ ቼልሲን ሻምፒዮን በማድረግ ትናንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል።
በውድድሩ ሁለቱን የማድሪድ ክለቦች በተመሳሳይ 4 ለ 0 በማሸነፍ ጭምር 16 ግቦችን በማስቆጠር በሚያስደንቅ ብቃት ለፍጻሜው የደረሰው ፒኤስጂ በመጨረሻም ለቼልሲ እጅ ሰጥቷል።
ባየርን ሙኒክ፣…
በባሕር ዳር ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በባሕር ዳር ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
መርሐ ግብሩን የአማራ ልማት ማሕበር (አልማ)፣ የባሕር ዳር ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የባሕር ዳር ከተማ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡
"ለአልማ እሮጣለሁ ማኅበራዊ ሃላፊነቴን እወጣለሁ"በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደው…
የክለቦች ዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በተገኙበት ዛሬ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳዩ ፒኤስጂ እና የእንግሊዙ ቼልሲ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት የክለቦች ዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፍጻሜ ጨዋታውን ለመመልከት በሜት ላይፍ ስታዲየም እንደሚታደሙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በአዲስ አቀራረብ 32 ቡድኖችን አሳትፎ ውድድሩን የጀመረው የ2025…
አንድሬ ኦናና ከቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታዎች ውጪ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በጉዳት ምክንያት ከቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታዎች ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
የ29 ዓመቱ ካሜሮናዊ ግብ ጠባቂ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከስድስት አስከ ስምንት ሳምንታት ድረስ ከሜዳ እንደሚርቅ ተዘግቧል፡፡
የኦናናን ጉዳት ተከትሎ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ሌላ ግብ…
ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንደማይሳተፍ ተረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዙ ክለብ ክሪስታል ፓላስ በሚቀጥለው የውድደር ዓመት በዩሮፓ ሊግ እንደማይሳተፍ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታወቀ፡፡
ንስሮች በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ማንቼስተር ሲቲን በማሸነፍ ሻምፒዮን የሆኑ ሲሆን በዩሮፓ ሊግ የሚሳተፉበትን እድልም አግኝተው ነበር፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ እድል…