Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኤ ሲ ሚላን ፓውሎ ፎኔስካን ከኃላፊነት አነሳ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያን ሴሪ ኤው ክለብ ኤ ሲ ሚላን አሰልጣኝ ፓውሎ ፎኔስካን ከኃላፊነት ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ክለቡ አሰልጣኙን ያሰናበተው ኤ ሲ ሚላን በትናንትናው ዕለት ከሮማ ጋር አንድ አቻ ከተለያየ በኋላ ነው፡፡ በሴሪ ኤው እንዲሁም በአውሮፓ መድረክ ቡድኑ እያስመዘገበ ያለው ደካማ እንቅስቃሴ ለስንብቱ ምክንያት መሆኑም ተገልጿል፡፡ ፓውሎ ፎኔስካ የቀድሞውን የቡድኑ አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊን በመተካት የማሰልጠን ኃላፊነቱን መረከባቸው ይታወሳል፡፡ ሆኖም ቡድኑ በውድድር ዓመቱ እያስመዘገባ…
Read More...

አሠልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጥሪው የቀረበው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አንደኛ ዙር ከዚምባብዌ ጋር በጥር ወር መጀመሪያ ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች…

ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስትል ዩናይትድ የሚያደርጉት ግጥሚያ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 19ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ ኦልድትራፎርድ ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል፡፡ ጨዋታው ምሽት 5 ሠዓት ላይ ሲደረግ በተደጋጋሚ ሽንፈት ጫና ውስጥ የሚገኘው የሩበን አሞሪም ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ዩናይትድ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡…

ማንቼስተር ሲቲ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለወራት በውጤት ቀውስ ውስጥ የቆየው ማንቼስተር ሲቲ ከ4 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በኋላ ሌስተር ሲቲን በማሸነፍ ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡ በገና በዓል ሰሞን ከሜዳቸው ውጭ ሌስተር ሲቲን የገጠሙት ሲቲዝኖቹ በሳቪኒሆ ሞሬራ እና ኤርሊንግ ሃላንድ ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡ በጨዋታው የመጀመሪያ ጎል ያስቆረው ብራዚላዊው…

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 6 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛው ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ሥድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በዚህም መሠረት 11 ከ30 ላይ ሌስተር ሲቲ በሜዳው የአምናውን ሻምፒየን ማንቼስተር ሲቲን ያስተናግዳል፡፡ እንዲሁም በተመሳሳይ ምሽት 12 ሠዓት ላይ ክሪስታል ፓላስ ከሳውዝ ሃምፕተን፣ ኤቨርተን ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ፉልሃም ከበርንማውዝ…

የአጭር፣ መካከለኛ ፣ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ የሜዳ ተግባራት እና የእርምጃ ውድድሮች በዚህ ወር ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ ፣ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ የሜዳ ተግባራት እና የእርምጃ ውድድሮች ከታሕሣሥ 22 እስከ 26 እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ ። በውድድሩ 21 ክለቦች፣ ሁለት ማሰልጠኛ ተቋማት እና አንድ አካዳሚን ጨምሮ 24 ተቋማት ይካፈላሉ ። በአጠቃላይ በውድድሩ 331 ሴቶች እና…

የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች ለተመልካች ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች ለተመልካች ክፍት እንዲሆኑ መወሰኑን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ እየተካሄዱ ሲሆን÷ የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ ላይ ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ በዚህ ዙር የሚደረጉ ጨዋታዎች በዝግ እንዲደረጉ ትናንት ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል።…