Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በለንደን ዳይመንድ ሊግ የ1 ማይል ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በለንደን ዳይመንድ ሊግ የ1 ማይል ሴቶች ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የቦታውን ክበረወሰን በማሻሻል አሸነፈች፡፡ ጉዳፍ ርቀቱን በ4 ደቂቃ ከ11 ሰኮንድ ከ88 ማይክሮ ሰኮንድ በመግባት ነው ያሸነፈችው፡፡ ጉዳፍ የገባችበት ሰዓት የርቀቱ የምንጊዜም ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ሲመዘገብ የቦታው ደግሞ ክበረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Read More...

ላሚን ያማል ጋር የደረሰው 10 ቁጥር ማልያ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አብዛኞቹ ክለቦች ትልልቅ ታሪክ የተሰራባቸውን ማልያዎች እንዲሁ በቀላሉ የትኛውም ተጫዋች እንዲለብሰው አይፈቅዱም፡፡ ትልልቅ ተጫዋቾች ለብሰውት ታሪክ ሰርተው ያለፉበትን ማልያ በአጋጣሚ የመልበስ ዕድል አግኝተው ለብሰው የተጫወቱ አንዳንድ ተጫዋቾች የማልያው ክብር እና ዝና ሲከብዳቸው ይስተዋላል፡፡ በስፔኑ ክለብ ባርሴሎና…

ኖኒ ማዱኬ አርሰናልን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቼልሲው የፊት መስመር ተጫዋች ኖኒ ማዱኬ በይፋ መድፈኞቹን ተቀላቅሏል፡፡ እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች እስከ ፈረንጆቹ 2030 በአርሰናል ቤት የሚያቆየውን የ5 ዓመት ኮንትራት ፈርሟል። አርሰናል ለተጫዋቹ ዝውውር 52 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ አድርጓል። ማዱኬ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውወር መስኮት ለአርሰናል…

ኢትዮጵያ ተጨማሪ የብርና ነሃስ ሜዳሊያዎች አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጨማሪ የብርና ነሃስ ሜዳሊያዎች አግኝታለች፡፡ በናይጄሪያ አቡኩታ እየተካሄደ በሚገኘው ሻምፒዮና ሁለተኛ ቀን ውሎ በ3ሺህ ሜትር ሴቶች ከ18 ዓመት በታች ውድድር ደስታ ታደለ 2ኛ እንዲሁም ብርነሽ ደሴ 3ኛ በመውጣት የብር እና ነሀስ ሜዳሊያ አስገኝተዋል፡፡…

ትኩረት የሳበው የሆንግ ኮንግ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሙዚየም

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሆንግ ኮንግ የተከፈተው የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሙዚየም በዓለም ዙሪያ ያሉ አድናቂዋቹን ትኩረት ስቧል፡፡ ሙዚየሙ የክርስቲያኖ ሮናልዶን የሁለት አስርት ዓመታት ድንቅ የእግር ኳስ ህይወት ጊዜያትን በተንቀሳቃሽ ምስል እና በፎቶ ያሳያል። በትናንትናው ዕለት የወጡ ምስሎች እንደሚያሳዩት…

ምህረት የለሹ ተከላካይ ያፕ ስታም

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከቴሪ ኦንሪ እስከ አለን ሺረር፣ ከማይክል ኦውን እስከ ፊሊፖ ኢንዛጊ በሜዳ ውስጥ እሱን በተቃራኒ መግጠም ምን ያህል ከባድ እንደሆነ በአደባባይ መስክረውለታል። የማንቼስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተጫዋች የነበረው የሀገሩ ልጅ ቫን ኒስትሮይ በልምምድ ሜዳም ቢሆን ያፕ ስታምን መግጠም ፈታኝ መሆኑን መናገሩ አይዘነጋም።…

የቼልሲው ግብ ጠባቂ ፔትሮቪች ለቦርንማውዝ ፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ግብ ጠባቂ ጆርጄ ፔትሮቭች በ25 ሚሊየን ፓውንድ ለቦርንማውዝ ፈረመ፡፡ በፈረንጆቹ 2023 ከኒው ኢንግላንድ ሪቮሉሽን በ14 ሚሊየን ፓወንድ ሰማያዊዎቹን የተቀላቀለው ሰርቢያዊው ግብ ጠባቂ፤ በተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ለፈረንሳዩ ክለብ ስትራስቡርግ በውሰት መጫወቱ ይታወሳል። የ25…