ስፓርት
ብሔራዊ ቡድኑ ከሱዳን አቻው ጋር የቻን ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ውድድር (ቻን) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
የሁለቱ ቡድኖች የቻን የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ቀን 11 ሰዓት በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል።
ጨዋታውን ለማከናወን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አስቀድሞ ወደ ሊቢያ ያቀና ሲሆን ለሁለት ቀናት በቤንጋዚ ልምምድ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።
Read More...
አርሰናል ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ ነጥቡን ወደ 33 አሳደገ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው አርሰናልን ያስተናገደው ክሪስታል ፓላስ 5 ለ 1 በሆነ ውጤት ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
የመድፈኞቹን ጎሎችን በ6ኛው እና 14ኛው ጄሱስ፣ በ38ኛው ሀቨርትዝ፣ በ60ኛው ማርቲኔሊ እንዲሁም በ84ኛው ደቂቃ ራይስ አስቆጥረዋል፡፡
ማሸነፋቸውን ተከትሎም ነጥባቸውን ወደ 33…
ማንቼስተር ሲቲ ዛሬም ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስቶንቪላ በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
በቪላ ፓርክ በተደረገው ጨዋታ የነገሡት አስቶንቪላዎች÷ ጆን ዱራን በ16ኛው እንዲሁም ሞርጋን ሮጀርስ በ65ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች ተጋጣሚያቸውን ረትተዋል፡፡
የማንቼስተር ሲቲን ከሽንፈት…
በሊጉ የበዓል ሰሞን መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ፤ክሪስታል ፓላስ ከአርሰናል ዛሬ ይጫወታሉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከአርሴናል ዛሬ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ።
በከፍተኛ የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ወደቪላ ፓርክ ተጉዞ ከቀኑ 9:30 ላይ ከአስቶን ቪላ ጋር በሚያከናውነው ጨዋታ ከባድ ፈተና እንደሚጠብቀው…
አትሌት ድርቤ በግራንድ ስላም ትራክ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ድርቤ ወልተጂ የግል የውድድር መድረክ በሆነው የግራንድ ስላም ትራክ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የኮንትራት ስምምነት ፈርማለች፡፡
በስምምነቱ መሰረት በ1 ሺህ 500 ሜትር ርቀት ላይ በመወዳደር የምትታወቀው አትሌት ድርቤ በ2025 በአሜሪካ በሚደረገው የግራንድ ስላም ትራክ ውድድር ላይ ትሳተፋለች፡፡…
ለማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት ለተጋለጡ 25 አትሌቶች የኤአይ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አትሌቲክስ 25 የተለያዩ ሀገራት አትሌቶች ራሳቸውን ከማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት እንዲከላከሉ የሚያስችል የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (ኤአይ) ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ተቋሙ ባደረገው የአራት ዓመታት ጥናት አትሌቶቹ ለከፋ የማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተገልጿል።
በመሆኑም የማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት…
ሪያል ማድሪድ የኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ ዋንጫን አነሳ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የ2024 የፊፋ ኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ ዋንጫን አንስቷል፡፡
ማድሪድ ዋንጫውን ለማንሳት የበቃው ከሜክሲኮው ክለብ ፓቹካ ጋር ያደረገውን የፍፃሜ ጨዋታ 3 ለ 0 በመርታት ነው፡፡
ኪሊያን ምባፔ፣ ሮድሪጎ እና ቪኒሺየስ ጁኒየር ደግሞ ግቦቹን ከመረብ ማሳረፋቸውን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡