Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ግራቨንበርች- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ግራቨንበርች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመባል ተመርጧል፡፡ የ23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ግራቨንበርች ከእንግሊዛዊው ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ቀጥሎ የዓመቱ ወጣት ተጨዋች ሽልማትን ያሸነፈ 2ኛው የሊቨርፑል ተጨዋች ሆኗል፡፡ ኔዘርላንዳዊው ግራቨንበርች በዚህ የውድድር ዓመት በሊጉ ባደረጋቸው 36 ጨዋታዎች አራት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡ በወንድማገኝ ጸጋዬ
Read More...

ድሬዳዋ ከተማ ባህር ዳር ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች አቤል አሰበ በጨዋታ እንዲሁም አስራት ቱንጆ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ የባህር ዳር ከተማን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ሙጂብ ቃሲም አስቆጥሯል፡፡…

ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ መድንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ራምኬል ጀምስ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት…

ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉበት የመላው አማራ ጨዋታዎች ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደሴ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 9ኛው መላው አማራ ጨዋታዎች ውድድር በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። ከግንቦት 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ “ስፖርት ለሰላም፤ ሰላም ለሁሉም” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ በቆየው ውድድር÷ በ19 የስፖርት አይነቶች ከ18 ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች መሳተፋቸው ተገልጿል።…

ሃሪ ኬን እና ዋንጫ የታረቁበት የውድድር ዓመት…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርሰናል አካዳሚ ተጫዋች በነበረበት ወቅት የስፖርት አቋም የለህም ተብሎ ተባርሯል፡፡ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነው፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ከአለን ሺረር በመቀጠል ሁለተኛ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ቢሆንም በሊጉ በቆየባቸው ዓመታት ግን ከዋንጫ ጋር መገናኘት አልቻለም። በቶተንሃም ሆትስፐር…

የኢትዮጵያ አትሌቶች ከትራክ ወደ ጎዳና ውድድሮች ፍልሰት …

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ወጣት አትሌቶች ወደ ጎዳና ውድድሮች እያመሩ መሆናቸው አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የዘርፉ ምሁራን ገለጹ። በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህርና የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ንጉሴ ጊቻሞ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ አትሌቶች በትራክ ውድድሮች ላይ ራሳቸውን በሚገባ…

የፍጻሜ ተፋላሚዎቹ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር …

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርን ያገናኘው ተጠባቂው የዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ በቢልባኦ ከተማ በሚገኘው ሳን ማሜስ ስታዲየም ይደረጋል፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ወጥ ብቃት ማሳየት የተሳነው ማንቼስተር ዩናይትድ፤ በዩሮፓ ሊግ አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ…