ስፓርት
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው የማንቼስተር ዩናይትድ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ የ2025/26 የውድድር ዘመን ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡
ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዓመቱ በ34 ጨዋታዎች 8 ግቦችን ሲያስቆጥር ÷ 20 ለግብ የሚሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን ደግሞ ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
Read More...
ማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክን በቋሚነት ሾመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክን በቋሚነት መሾሙን ይፋ አድርጓል፡፡
አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት እስከ ፈረንጆቹ 2028 ድረስ የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡
የ44 ዓመቱ አሰልጣኝ ቡድኑን በጊዜያዊነት እየመራ ከሁለት ዓመታት በኋላ ወደ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መድረክ መመለስ ችሏል፡፡…
የራሱን ታሪክ የደገመው አርሰናል…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል በስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ እየተመራ የ2025/26 የውድድር ዓመት የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወቃል፡፡
ባለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አርሰናል በዚህ ዓመት ሻምፒዮን በመሆን ከዚህ ቀደም ራሱ ፅፎት የነበረውን ታሪክ መድገም ችሏል፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ…
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ወደ ድል ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች መስፍን ታፈሰ (2) እና ኤፍሬም ታምራት (በራሱ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከሦስት ተከታታይ…
የቪላን የ30 ዓመት የዋንጫ ጥም የቆረጡት የዩሮፓ ሊግ አለቃ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አስቶን ቪላ ከ30 ዓመታት የዋንጫ ጥበቃ በኋላ ትናንት ምሽት የጀርመኑን ክለብ ፍሬቡርግ በማሸነፍ የዩሮፓ ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡
አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬ ላለፉት ዓመታት "የምንፈልገውን የሚያውቅ ምርጥ አሰልጣኝ አግኝተናል" በሚል በቪላ ደጋፊዎች ሲዘመርላቸው ቆይተዋል፡፡
ኡናይ ኢምሬ የአሰልጣኝነት ስራን የጀመሩት…
ገደኛው ቪክቶር ዮከሬሽ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቪክቶር ኢናር ዮከሬሽ የተወለደው በአውሮፓዊቷ ሀገር ስዊዲን በፈረንጆቹ 1998 ነው፡፡
በፈረንጆቹ 2015 በሀገሩ ክለብ ብሮማፖጅካርና የመጀመሪያ ጨዋታውን በማድረግ የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ህይወትን የጀመረው ቪክቶር÷ በብራይተን፣ ኮቨንተሪ ሲቲ እና ስዋንሲ ሲቲ በመሳሰሉ የእንግሊዝ ክለቦች ያልተሳካ ጊዜን አሳልፏል፡፡…
በኤሲሚላን ራሱን ለዓለም ያሳየው አንድሪያ ፒርሎ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጣሊያናዊው የኤሲሚላን የቀድሞ ኮከብ አንድሪያ ፒርሎ ከምንጊዜም ምርጥ የመሐል ሜዳ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው፡፡
በፈረንጆቹ 1979 በዛሬዋ ዕለት የተወለደው አንድሪያ ፒርሎ የእግር ኳስ ሕይወቱን የጀመረው በሀገሩ ክለብ ብሬሺያ ነው፡፡
ከምንጊዜም ታላላቅ የመሐል ሜዳ ተጫዋች መካከል አንዱ የሆነው ፒርሎ በእይታው፣…