Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሜሲ እና ምባፔ የምንጊዜም የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ለመሆን…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንጆቹ 1930 መደረግ በጀመረው የዓለም ዋንጫ ውድድር ጀርመናዊው ሚሮስላቭ ክሎስ የመድረኩን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃን እየመራው ይገኛል፡፡ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ኮከብ ሚሮስላቭ ክሎስ በዓለም ዋንጫ ውድድር 24 ጨዋታዎችን አድርጎ 16 ግቦችን በማስቆጠር የዓለም ዋንጫ የምን ጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃን እየመራ ይገኛል፡፡ ሚሮስላቭ ክሎስ በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ሀገሩ ጀርመንን ወክሎ የተጫወተ ሲሆን÷ አንድ ጊዜ በመድረኩ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ የብራዚል…
Read More...

ሪያል ማድሪድ ኩኩሬላን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ማርክ ኩኩሬላን ከቼልሲ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ ስፔናዊው የግራ መስመር ተጫዋች በሪያል ማድሪድ ቤት እስከ ፈረንጆቹ 2032 ድረስ የሚያቆየውን ውል ነው የተፈራረመው፡፡ ሪያል ማድሪድ ለ27 ዓመቱ ተጫዋች 55 ሚሊየን ዩሮ እና እየታየ የሚጨመር 5 ሚሊየን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ የሚከፍል…

ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ለሲዳማ ቡና የማሸነፊያ ግቦቹን ያሬድ ባየህ እና ብርሃኑ በቀለ…

ለዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ስፖርት ውድድሮች ተመራጭ የሆነችው አዲስ አበባ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስፖርቱ ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረትና ባከናወናቸው ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ምክንያት መዲናዋ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች በስፋት የሚስተናገዱባት ቀዳሚ ተመራጭ የስፖርት ማዕከል መሆን ችላለች፡፡ ባለፉት ዓመታት በከተማዋ የተገነቡት ከ1 ሺህ 580 በላይ የሕዝብና የወጣቶች ስፖርት…

የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ያዘጋጁት የ2026 ዓለም ዋንጫ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡ የውድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ካናዳ እና አሜሪካ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በዛሬው ዕለት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡ ምድብ ሁለት ላይ የምትገኘው ካናዳ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ከቦስኒያ ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡…

በሁሉም የዓለም ዋንጫ የተሳተችፈው ብራዚል…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚል በዓለም ዋንጫ መድረክ ከምስረታው ጀምሮ በእያንዳንዱ ውድድር ላይ በመሳተፍ ቀዳሚዋ እና ብቸኛዋ ሀገር ናት፡፡ የዓለም ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀው ትልቁ የሀገራት ውድድር የዓለም ዋንጫ በፈረንጆቹ 1930 ነው መደረግ የጀመረው፡፡ ብራዚል ከዓለም ዋንጫ ጅማሮ አንስቶ እስካሁን ድረስ በሁሉም የዓለም ዋንጫ የተሳተፈች ሲሆን…

23ኛው የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ ያዘጋጁት የ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በሜክሲኮ ሲቲ ስታዲየም መካሄድ ጀምሯል፡፡ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ሀገራት የሚያዘጋጁት ሲሆን ÷ በመርሐ ግብሩ 48 ሀገራት ይሳተፋሉ፡፡ በአጠቃላይ 1 ሺህ 248 ተጫዋቾች የሚሳተፉበት ውድድሩ÷…