ስፓርት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ 9ኛ ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 9ኛ ጨዋታውን በዛሬው ዕለት ከጊኒ ቢሳው ጋር ያደርጋል፡፡
ከ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑን አስቀድሞ ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መርሐ ግብር ለማሟላት ነው ጨዋታውን የሚያካሂደው፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በማጣሪያው ካደረጋቸው 8 ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ሲያሸንፍ ÷ በሶስቱ አቻ እንዲሁም በአራቱ ደግሞ ተሸንፏል፤በዚህም በ6 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ጊኒ ቢሳው ካደረጋቸው…
Read More...
በዲዮጎ ጆታ ስም ለማህበረሰብ ተኮር ተግባራት ከ225 ሺህ ፓውንድ በላይ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊቨርፑል በዲያጎ ጆታ እና በወንድሙ አንድሬ ጆታ ስም ለሚከናወኑ ማህበረሰብ ተኮር ተግባራት የሚውል ከ225 ሺህ ፓውንድ በላይ ገቢ መሰብሰቡን ይፋ አድርጓል፡፡
ሊቨርፑል ገቢውን የሰበሰበው ለዲያጎ ጆታ መታሰቢያ ከተዘጋጁ ህትመቶችና ቲሸርቶች ሽያጭ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ገንዘቡ በሊቨርፑል ፋውንዴሽን በኩል ለዲያጎ ጆታ…
በሜዳ ውስጥ ውዝግቦች መሃል የማይታጣው ኮከብ ዲያጎ ኮስታ…
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በስታምፎርድ ብሪጅ የሚወደድ እና በሜዳ ላይ በሚኖሩ ውዝግቦች መሃል የማይጠፋ ኮከብ ነው የቼልሲ የቀድሞ ተጫዋች ዲያጎ ኮስታ፡፡
በአስፈሪ ቁጣው የሚታወቀው ዲያጎ ኮስታ ሜዳ ላይ ከሚያሳየው ድንቅ ብቃት በተጨማሪ በሃይለኛነቱ እና ሜዳ ላይ በሚኖሩ አለመግባባቶች ውስጥ ግንባር ቀደም መሆኑ ይታወሳል፡፡
ዲያጎ ኮስታ…
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በጎዳና ላይ ውድድሮች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የጎዳና ላይ ውድድሮች ድል ተቀዳጅተዋል።
በሮማንያ በተደረገ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን፥ በወንዶች አትሌት ከሀሪ ቤጂጋ እንዲሁም በሴቶች አትሌት መዲና ኢሳ በቀዳሚነት አጠናቅቀዋል።
በስፔን…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 5 ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በዚህ መሰረትም ቀን 10 ሰዓት ላይ አስቶንቪላ ከበርንሌይ፣ ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ፣ ኒውካስል ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት እንዲሁም ዎልቭስ ከብራይተን ይጫወታሉ፡፡
በተጨማሪም ምሽት 12፡30 ማንቼስተር ሲቲ ወደ ለንደን…
በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ቼልሲ ሊቨርፑልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠባቂ ጨዋታ ቼልሲ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ምሽት 1፡30 ላይ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ሊቨርፑልን ያስተናገደው ቼልሲ ካሴዶ እና ኢስቲቫኦ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
የሊቨርፑልን ብቸኛ…
ቶተንሀም ሊድስ ዩናይትድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሀም ሆትስፐር ሊድስ ዩናይትድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ቀን ከ8:30 ላይ በሊድስ ሜዳ ኢላንድ ሮድ በተካሄደው ጨዋታ ቶተንሃም ድል ቀንቶታል።
በዚህም ፈረንሳዊው ማቲይስ ቴል እና ጋናዊው ሞሀመድ ኩዱስ የቶተንሀምን ግቦች አስቆጥረዋል።…