Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም ጥላሁንና አማኑኤል ኤርቦ አስቆጥረዋል፡፡ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ኪሩቤል ወንድሙ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ ባሕር ዳር ከተማና አዳማ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
Read More...

የሲቲው አማካይ ሮድሪጎ ሄርናንዴዝ ከውድድር ዓመቱ ተሳትፎ ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው የማንቼስተር ሲቲ አማካይ ሮድሪጎ ሄርናንዴዝ ባጋጠመው የጉልበት ጉዳት ከ2024/25 የውድድር ዓመት ተሳትፎ ውጪ መሆኑን ክለቡ አስታውቋል፡ ተጫዋቹ ጉዳቱን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ከአርሰናል ጋር ባደረገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ነበር፡፡ የ28 ዓመቱ የዩሮ 2024 አሸናፊ ሮድሪ…

በፕሪሚየር ሊጉ ስሑል ሽረ እና ሐዋሳ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ስሑል ሽረ እና ሐዋሳ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ስሑል ሽረ ፋሲል አስማማው በ48ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ሲመራ ቢቆይም÷ የስሑል ሽረው መሐመድ ሱሌይማን በ93ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ ሐዋሳ ከተማ ነጥብ እንዲጋራ አስችሎታል፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ…

በኒውዮርክ በተካሄደው የ800 ሜትር ውድድር ፅጌ ዱጉማ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒውዮርክ በተካሄደው የ800 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ አሸንፋለች፡፡ አትሌቷ ርቀቱን 1 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ 3 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲዬም ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት 3 ሠዓት ከ30 ላይ ሐዋሳ ከተማ ከስሁል ሽረ እንዲሁም 10 ሠዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ይጫወታሉ፡፡ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ደግሞ ባሕር ዳር ከተማ እና አዳማ ከተማ…

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ። በድሬዳዋ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ያሬድ ብርሃኑ ባስቆጠራት ግብ ሲመራ ቢቆይም፤ ፋሲል ከነማ ቢኒያም ላንቃሞ ከእረፍት መልስ ባስቆጠራት ግብ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።…

ዋሊያዎቹ የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ኮትዲቯር ላይ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር የሚያደርጋቸውን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ 3ኛ እና 4ኛ የምድብ ጨዋታዎች ኮትዲቯር ላይ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ዋሊያዎቹ 3ኛውን ጨዋታ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 1 ሠዓት ላይ ጊኒ የሜዳ ጨዋታዋን ለማድረግ ባስመዘገበችው በኮትዲቯር ያሞሱክሩ በሚገኘው…