Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ወላይታ ድቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሣምንት ጨዋታ ወላይታ ድቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 2 አሸነፈ። ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወላይታ ድቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ጌታሁን ባፋ (በራስ ላይ)፣ ተስፋዬ መላኩ እና ካርሎስ ዳምጠው ባስቆጠሯቸው ግቦች ድል አድርጓል። በዚህም በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታው ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ እዮብ ገብረማሪያም እና አቤል ሀብታሙ አማካኝነት ሁለት ጎሎች አስቆጥረዋል።
Read More...

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ5ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከአርሰናል ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል ፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ቀን 10 ሰዓት ላይ ብራይተን ሆቭ አልቢዮን እና ኖቲንግሃም ፎረስት በአሜክስ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ ምሽት 12፡30 ላይ ደግሞ ማቼስተር ሲቲ ከአርሰናል በኢቲሃድ ስታዲየም…

 ባሕር ዳር ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሣምንት ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ባሕር ዳር ከተማ ተጋጣሚውን ያሸነፈው ፍጹም ዓለሙ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራት ጎል ነው፡፡ ቀደም ብሎ በወልቂጤ ከነማ እና መቻል መካከል ሊደረግ የነበረው ጨዋታ የወልቂጤ ከተማ እግር…

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ክሪስታል ፓላስ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ክሪስታል ፓላስ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡ በኳስ ቁጥጥር ማንቼስተር ዩናይትድ ተሽሎ በተገኘበት ጨዋታ ምንም ጎል ሳይቆጠር በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

አትሌት ሰውመሆን የመጀመሪያ ዙር የተሳካ የዓይን ቀዶ ጥገና አድርጓል- ፌደሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በልምምድ ላይ ሳለ በደረሰበት ጥቃት ግራ ዓይኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው አትሌት ሰውመሆን አንተነህ የመጀመሪያ ዙር የተሳካ የዓይን ቀዶ ጥገና ሕክምና ማድረጉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡ ጉዳቱን ተከትሎ በሀገር ውስጥ ሕክምና ሲከታተል መቆየቱን እና ለተሻለ ሕክምና ወደ ሕንድ ቼይና ማቅናቱን…

ሊቨርፑል፣ ቶተንሃም፣ ፉልሃም እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን ረቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ5ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተመሳሳይ 11 ሠዓት ላይ ሥድስት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ሊቨርፑል በርንማውዝን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ቶተንሃም ብሬንትፎርድን፣ ፉልሃም ኒውካስልን፣  አስቶንቪላ ዎልቭስን ተመሳሳይ በሆነ ውጤት 3 ለ 1 መርታት ችለዋል፡፡ እንዲሁም ሳውዝሃምተን ከኢፕስዊች ታውን እና…

ቼልሲ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበበ፣ መስከረም 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ5ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ከሜዳው ውጭ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡ 8 ሠዓት ከ30 ላይ በተደረገው ጨዋታ ኒኮላስ ጃክሰን የቼልሲን ሁለት ጎሎች ሲያስቆጥር÷  ቀሪዋን አንድ ጎል ደግሞ ኮል ፓልመር  ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡ የሊጉ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ 11 ሠዓት ላይ አስቶንቪላ…