Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ መድንና አርባምንጭ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሣምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድንና አርባምንጭ ከተማ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያዩ፡፡ በሌላ በኩል ምሽት 1 ሠዓት ላይ ሊደረግ የነበረው የወልቂጤ ከተማ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ÷ የወልቂጤ ከተማ ክለብ ማሟላት የሚጠበቅበትን ባለማሟላቱ ምክንያት ንግድ ባንክ በፎርፌ 3 ነጥብ አግኝቷል፡፡ ወልቂጤ ከተማ ባለፈው ሳምንትም ከመቻል ጋር መጫወት ሳይችል ቀርቶ በፎርፌ መሸነፉ ይታወሳል፡፡
Read More...

የ2024 የአፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024 የአፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የፊታችን ጥቅምት ወር ላይ ይካሄዳል፡፡ ከጥቅምት 2 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በሚካሄደው ሻምፒዮና ላይ ከ300 በላይ ስፖርተኞችና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡ በውድድሩ የሚያሸንፉ ስፖርተኞች የ25…

ራፋዬል ቫራን ጫማ ሰቀለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪያል ማድሪድ እና ማንቼስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተከላካይ ሥፍራ ተጫዋች ራፋዬል ቫራን እግር ኳስ ማቆሙን አስታውቋል፡፡ ቫራን ባለፈው ክረምት የዝውውር መስኮት ማቼስተር ዩናይትድን በመልቀቅ የጣሊያኑን ኮሞ እግር ኳስ ክለብ መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡ በአዲሱ ክለቡ በነበረበት ጊዜ ያጋጠመው ጉዳት ተከትሎም በ31 ዓመቱ ጫማ…

ማንቼስተር ዩናይትድ የኦልድትራፎርድ ስታዲየምን ሊያድስ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ አንጋፋውን የኦልድትራፎርድ ስታዲም በሁለት ቢሊየን ፓውንድ ወጪ ሊያድስ መሆኑን አስታወቀ፡፡ እድሳቱ ሲጠናቀቅ የስታዲየሙ ተመልካች የመያዝ አቅም ከ100 ሺህ በላይ እንደሚሆን ተገልጿል። እንዲሁም ዕድሳቱ ሲጠናቀቅ በዓመት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።…

በፕሪሚየር ሊጉ ስሑል ሽረ አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሣምንት ጨዋታ ስሑል ሽረ አዳማ ከተማን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የስሑል ሽረን የማሸነፊያ ግቦች አሌክስ ኪታታ፣ አላዛር አድማሱ እና ኤልያስ አሕመድ (በፍጹም ቅጣት ምት) አስቆጥረዋል፡፡ የአዳማ ከተማን ግቦች ደግሞ…

ሰሜን ኮሪያ የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫን አነሳች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ለሶስተኛ ጊዜ የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫን አንስታለች፡፡ ይህም ከዚህ ቀደም ዋንጫውን ሶስት ጊዜ ማንሳት ከቻሉት ጀርመን እና አሜሪካ ጋር ታሪክ እንዲጋሩ አስችሏታል። ሰሜን ኮሪያ በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ጃፓንን 1 ለ 0 በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን መሆን…

በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሣምንት መርሐ-ግብር የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ። በዚሁ መሠረት አዳማ ከተማ ከስሑል ሽረ 10 ሠዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይጫወታሉ። ስሑል ሽረ ዘንድሮ ዳግም ወደ ሊጉ ውድድር መመለሱ የሚታወስ ሲሆን÷ አዳማ ከተማ ባለፈው የውድድር ዘመን 44 ነጥብ በመያዝ 7ኛ ደረጃን ይዞ…