Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ስታዲየም በተጀመረው የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ አርባምንጭ ከተማን አሸንፏል። ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ቻርልስ ሙሰጌ እና መሐመድኑር ናስር ባስቆጠሯቸው ግቦች አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል። አርባምንጭ ከተማን ከሽንፈት ያላዳነውን ብቸኛ ግብ አህመድ ሁሴን አስቆጥሯል። ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው የሊጉ መክፈቻ ጨዋታ ሃድያ ሆሳዕና መቐለ 70 እንደርታን…
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ሃድያ ሆሳዕና መቐለ 70 እንደርታን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ስታዲየም ተጀምሯል፡፡ ቀን 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ ሃድያ ሆሳዕና መቐለ 70 እንደርታን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሃድያ ሆሳዕናን ብቸኛ የማሸፊያ ግብ ሄኖክ አርፍጮ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡ የሊጉ…

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ስታዲየም ይጀመራል። በዚህ መሰረትም መቐለ 70 እንደርታ እና ሃዲያ ሆሳዕና ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም የሊጉን የመክፈቻ ጨዋታ ያካሂዳሉ፡፡ የሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብ ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ…

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት መርሐ ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት እና የማጠቃለያ መርሐ ግብር በድሬደዋ ከተማ ተካሂዷል። በዕለቱ በ7 ዘርፍ የዓመቱ ኮከቦች የተሸለሙ ሲሆን ፥ ለተሳታፊ ክለቦች እና ባለሜዳዎች የገንዘብ ክፍፍል ተደርጓል። በዚህ መሰረትም የውድድር አዘጋጅ ባለሜዳዎች አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ 4 ሚሊየን…

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ለተሳተፉ አትሌቶች የዕዉቅናና ሽልማት መርሐ-ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ለተሳተፉ አትሌቶች የዕውቅና እና የሽልማት መርሐ ግብር አካሄደ። ታምራት ቶላ በማራቶን ብቸኛ ወርቅ በማስገኘቱ 2 ሚሊየን ብር ሲሸለም፥ በውድድሩ የብር ሜዳሊያ ያስገኙት ትዕግሥት አሰፋ፣ ፅጌ ድጉማና በሪሁ አረጋዊ እያንዳንዳቸው 1 ሚሊየን ብር ተበርክቶላቸዋል።…

ሮማ አሰልጣኝ ዳንዔል ዲ ሮሲን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያኑ ክለብ ሮማ አሰልጣኝ ዳንዔል ዲ ሮሲን ከኃላፊነታቸው ማንሳቱን አስታውቋል፡፡ አሰልጣኙ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ሮማን ስኬታማ ማድረግ አልቻሉም በሚል ነው፡፡ ከአደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ሦስቱን በአቻ አንዱን በሽንፈት ማጠናቀቃቸውም ዲ ሮሲ እንዲሰናበቱ አድርጓል ተብሏል፡፡ እስከ አሁን ያለውን ውጤት ተከትሎም…

ብራዚላዊው ታዳጊ ኤንድሪክ በሪያል ማድሪድ መለያ በዕድሜ ትንሹ የቻምፒዮንስ ሊግ ግብ አስቆጣሪ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ታዳጊ ኤንድሪክ ትናንት ምሽት ስቱትጋርት ላይ ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ በሪያል ማድሪድ ታሪክ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በትንሽ ዕድሜ ግብ አስቆጣሪነት ክብረወሰን ባለቤት ሆኗል፡፡ ኤንድሪክ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የብራዚሉን ክለብ ፓልሜራስን በመልቀቅ ነጭ ለባሾቹን (ማሬንጌዎቹን) መቀላቀሉ ይታወቃል፡፡…