ስፓርት
የስፖርቱን ከዋክብት ያስደነገጠው የዲያጎ ዦታ ድንገተኛ ህልፈት…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ዲያጎ ዦታ እና በወንድሙ ድንገተኛ ህልፈት በርካታ የስፖርቱ ከዋከብቶችና የዓለም የስፖርት ቤተሰቦች ሀዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
የብሔራዊ ቡድን አጋሩ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፥ በተጫዋቹ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡
ከዦታ ጋር ከሳምንታት በፊት አብረን ነበርን ያለው ፖርቹጋላዊው ኮከብ፥ ዛሬ የተፈጠረውን ግን ለማመን ይከብዳል፥ ለባለቤቱ ለልጆቹ፣ ለቤተሰቦቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መፅናናትን እመኛለሁ ሲል የሀዘን መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
በተመሳሳይ…
Read More...
ቼልሲ ጆአዎ ፔድሮን ከብራይተን አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የብራይተኑን የፊት መስመር ተጫዋች ጆአዎ ፔድሮን በይፋ አስፈርሟል፡፡
ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ፔድሮ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ቤት እስከ ፈረንጆቹ 2032 የሚያቆውን ኮንትራት ተፈራርሟል፡፡
ቼልሲ ለፔድሮ ዝውውር 55 ሚሊየን ፓውንድ በቀጥታ የሚከፈል እና እየታየ የሚጨመር 5…
ከተቹት ውድድር የተሰናበቱት ፔፕ ጋርዲዮላ …
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የክለቦች ዓለም ዋንጫ ውድድር በተለያዩ አካላት በርካታ ትችት እየተሰነዘረበት ይገኛል፡፡
ውድድሩን ሲተቹ ከነበሩት መካከል የማንቼስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አንዱ ቢሆኑም በሳዑዲው ክለብ አልሂላል ተሸንፈው ከውድድሩ ተሰናብተዋል፡፡
በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው…
ሞናኮ አንሱ ፋቲን በውሰት አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ ስፔናዊውን የፊት መስመር ተጫዋች አንሱ ፋቲን በውሰት ውል አስፈርሟል፡፡
ሞናኮ ስፔናዊውን የፊት መስመር ተጫዋች በ11 ሚሊየን ዩሮ የመግዛት አማራጭ ባካተተ የውሰት ውል ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡
በ2024/25 የውድድር ዓመት አንሱ ፋቲ ለባርሴሎና በሁሉም ውድድር 10 ጨዋታዎች ላይ ተሳትፏል፡፡…
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በተለያዩ ጉዳዮች ውሳኔዎችን አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በዚሁም የሲዳማ ቡና ስፖርት ከለብ የታገዱ ተጫዋቾችን በማሰለፍ ያሸነፈው የኢትዮጵያ ዋንጫ በፎርፌ ተሸናፊ ሆኖ ዋንጫው ለወላይታ ድቻ ተመላሽ እንዲደረግ እና የወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ…
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ …
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ገብረመድህን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ስማቸውን በደማቁ ማጻፍ ከቻሉ አሰልጣኞች መካከል ከቀዳሚዎቹ አንዱ ነው፡፡
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ተብሎ መመረጡ አይዘነጋም፡፡
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ኢትዮጵያ መድን…
ፒኤስጂ ከሊዮኔል ሜሲው ኢንተር ማያሚ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር የፈረንሳዩ ፒኤስጂ ከሊዮኔል ሜሲው ኢንተር ማያሚ የሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይጠበቃል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ጨምሮ የሶስትዮሽ ዋንጫ አሸናፊው ፒኤስጂ ምድቡን በ6 ነጥብ የበላይ ሆኖ ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን በውድድሩ የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ተሰጥቶታል፡፡…