የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ለሶስት ቀናት ሲያደረጉት የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ለሶስት ቀናት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሲያደረጉት የነበረው ውይይት ዛሬ ተጠናቀቀ።
በሶስት ቀን ውይይቱ ላይ የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት በተገኙ ድሎች ፣ በታዩ ክፍተቶችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በዚህም የተገኘውን ድል ለመጠበቅ እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ አገራዊ እና ክልላዊ ስራዎችን በመለየት በተቀናጀ መንገድ ለመፈፀም እንሰራለን ብለዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በመዝጊያው ላይ እንደተናገሩት፥ ከድሉ በኋላ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች በሰላምና በልማት ስራ ላይ የጎላ ተፅእኖ እንዳያሳርፉ በንቃት እና በትጋት መስራት ይገባል ብለዋል።
ህዝቡም እንደ ወትሮው ሁሉ ከመንግሥት ጎን ተሰልፎ የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
አክለውም አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የክልሉ መንግስት ባደረገው ሰፊ ጥረት አበረታች ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም፥ በአሁኑ ወቅት የበልግ ዝናብ በክልሉ ባለመዝነቡ ከተከሰተው ድርቅ ህዝብና እንሰሳትን ለመታደግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም መረባረብና አመራሩ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎትን መስጠት አለበት ብለዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን በበኩላቸው፥ ሀገር ለማሻገር በሚደረጉ ውይይቶች ላይ በየደረጃው የሚገኘው ህዝብና ምሁራን ተሳትፎ ከፍተኛ መሆን አለበት ብለዋል።
አመራሩ ለህዝቡ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆን አለበትም ነው ያሉት።
የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ ፥ በክልሉ የተገኙ ሁለንተናዊ ድሎችን ጠብቆ በማስፋትና ወደዘላቂ ልማት በማሸጋገር እንዲሁም በድህረ ጦርነት ሊመጡ የሚችሉ የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ክፍተቶችን በብቃት ለመወጣት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የህግ ማስከበር ዘመቻ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በሶማሌ ክልል በኩል ኢትዮጵያን ከሶስት አገራት ጋር የሚያዋሰነውን በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች የሚሆን ድንበር በንቃት እየጠበቀ የሚገኘው የክልሉ ፀጥታ ሀይል የኢትዮጵያ ሉአላዊ ድንበር እንዳይደፈር እየሰራ ያለው ስራ የበለጠ ተጠንክሮ እንዲቀጥል አመራሩ በትኩረት እንደሚሰራ በመድረኩ ተገልጿል።
አገር የማፍረስ አላማ በመያዝ በአሸባሪው ሀይል የተከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስ በተደረገው የሕልውና ዘመቻ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በአንድነት ተሰልፎ ባደረጉት ሁለንተናዊ ርብርብ በተገኘው ድል ሳንዘናጋ ወቅቱ የሚጠይቀውን ሃላፊነት ለመወጣትም እንደተዘጋጁ መግለፃቸውን ከክልሉ ብዙሃን መገናኛ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!




+4
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share