Fana: At a Speed of Life!

ግብጽ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት አስመዘገበች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብጽ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት አስመዘገበች።

የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሟቹ የ60 አመት ጀርመናዊ ሲሆኑ፥ ከሳምንት በፊት ነበር ግብጽ የገቡት።

ግለሰቡ ግብጽ ከገቡ በኋላ በቀይ ባህር ዳርቻ መዝናኛ ሁርጋዳ ሆስፒታል የህክምና ክትትል ተደርጎላቸዋል።

ሚኒስቴሩ በአንድ ቀን ብቻ 45 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን ገልጿል፤ ይህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 48 ያደርሰዋል ነው የተባለው።

የቫይረሱ ተጠቂዎች የመርከብ ጉዞ ያደረጉ እንደነበሩም ተገልጿል።

አሁን ላይም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ክፍል እንዲቆዩ መደረጉን አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የተገኘባቸው ሃገራት ግብፅን ጨምሮ 9 ሲሆኑ፥ አልጀሪያ 17፣ ሴኔጋል 4፣ ደቡብ አፍሪካ 3፣ ሞሮኮ 2፣ ካሜሮን 2፣ ቱኒዚያ 1፣ ቶጎ 1 እና ናይጀሪያ 1 ሰው በቫይረሱ ተይዘዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ እና ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.