ኢትዮጵያ እና እስራኤል በስፖርት፣ በባህልና በኪነ ጥበብ ዘርፍ ተቀራርቦ ለመሥራት መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር አቶ አለልኝ አድማሱ ጋር ሀገራቱ በስፖርት፥ በባህል እና በኪነጥበብ ዘርፍ ተቀራርቦ ለመስራት በሚያስችሏው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
አቶ ቀጄላ መርዳሳ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ በእስራኤል አገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ጋር በደምና ታሪክ የተቆራኙ ናቸው፡፡
የእስራኤል አምባሳደር አቶ አለልኝ አድማሱ÷ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤሎች ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ታሪካቸውን ለመመልከት በአዲስ አበባ የባህል ማዕከል መገንባት ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በባህል ልውውጥ፣ በስፖርት እና በኪነ ጥበብ ተቀራርበው እንዲሠሩ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም እንደሚያስፈልግና ሰነድም እንዲዘጋጅ ከስምምነት ላይ መደረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ እና እስራኤል ተደጋግፈው እንዲሠሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊው እገዛ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!