ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ወንጀሎችን በጋራ መከላከልና የደህንነት መረጃ መለዋወጥ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መከሩ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያየ።
የልዑካን ቡድኑ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጉን አምባሳደር ሬድዋን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
በዚህ ወቅትም ሀገራቱ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል፣ ትብብርን ማሳደግ እና የደህንነት መረጃ መለዋወጥ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!