Fana: At a Speed of Life!

ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት አሰራርን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት አሰራርን ዛሬ ይፋ አደረገ።

አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላን ጨምሮ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

የኤሌክትሮኒክ አሰራሩ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለሙያዎች ትብብር የለማ ነው ተብሏል።

አሰራሩ በሚኒስቴሩ የሚሰጡ 10 አገልግሎቶችን በኦንላይን ማግኘት የሚያስችል ሲሆን÷ በአማርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋ አገልግሎት ያቀርባል ነው የተባለው።

ደንበኞች www.eservices.gov.et በሚለው ገብተው አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ፥ በአሰራሩ አገልግሎት መሰጠት ከጀመሩ 25 የመንግስት ተቋማት ዝርዝር መካከል በአገልግሎት፣ በአገልግሎት አቅራቢ አሊያም በርዕስ ማግኘት የሚፈልጉትን አገልግሎት መምረጥ ይችላሉ ተብሏል።

ለተገልጋዮች አዋጭ ዘርፉን ለመለየትና ለመገናኛ ብዙሃን የአምራች ዘርፉን መረጃ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል የኢንዱስትሪ መረጃ ስርዓትም በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚህ ወቅት እንደገለጹት ፥ አሰራሩ ግልጽ፣ ተደራሽ፣ ወጪ ቆጣቢና ከብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት ያስችላል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በበኩላቸው ፥ የመንግስት አገልግሎቶችን በአይሲቲ መደገፍ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እንዳለው በመገንዘብ ተቋማት አገልግሎታቸውን ዲጂታላይዝ እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኤሌክትሮኒክ አገልግሎት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ይፈራረማሉ መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.