Fana: At a Speed of Life!

በነሐሴ  የመጨረሻዎቹ 10 ቀናት የክረምቱ ዝናብ መቀነስ ያሳያል -ኢንስቲትዩቱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነሐሴ የመጨረሻዎቹ 10 ቀናት የክረምቱ ዝናብ መቀነስ የሚያሳበት ጊዜ መሆኑን የብሄራዊ ሜትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከነሐሴ 21-እስከ ነሐሴ 31 ድረስ የሚኖረውን የአየር ሁኔታ  አስታውቋል፡፡

በዚህም በመደበኛው ሁኔታ የክረምት ዝናብ ከሰሜን ኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች ላይ ከነሐሴ  መጨረሻዎቹ 10 ቀናት ጀምሮ ቀስ በቀስ የመቀነስ አዝማሚያ የሚያሣይበት ጊዜ መሆኑን አመላክቷል፡፡

በምስራቅና በደቡብ ደጋማ ሥፍራዎች  ደግሞ የክረምቱ ዝናብ  እየተስፋፋ ይሄዳል ነው የተባለው።

በመጪዎቹ  11 ቀናት ውስጥ የተተነበዩት የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የክረምት ዝናብ  በሰሜን፣ በሰሜን ምሥራቅ፣ በምሥራቅ በመካከለኛውና በምዕራብ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ በመካል በሚኖረው ጠንካራ የፀሐይ ሀይል በመታገዝ ከሚፈጠረው የደመና ክምችት ከባድ መጠን ያለው ዝናብ  ሊኖር እንደሚችል ከብሔራዊ ሜትዎሮሎጂ  ኢንስቲትዩት  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.