Fana: At a Speed of Life!

የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኞች የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሰን ተሻጋሪ የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች በአጋሮ ከተማ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በይፋ አስጀምረዋል፡፡

መርሐ ግብሩ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የተጀመረው፡፡

በዛሬው መርሐ ግብር ከ 5 ሺህ በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን÷ የደም ልገሳና የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት እድሳትም ተከናውኗል፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት÷ በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ በየጊዜው በተሳትፎም ሆነ በስራ ዘርፍ እያደገ ነው ብለዋል፡፡

ዘንድሮም በአረንጓዴ ዐሻራ እና ማዕድ ማጋራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡

ተግባራቱ ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ብሔራዊ የወጣቶች በጎ ፈቃድ ፖሊሲ ተቀርፆ ወደ ተግባር እንዲገባ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶቹ እስከ ፊታችን ሐምሌ 5 በሚቆየው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች ሁሉ የአረንጓዴ ዐሻራ ማሳረፍ ተግባር እንደሚያከናውኑ ተገልጿል፡፡

በጎህ ንጉሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.